Connect with us

#ወይ_አዲስአበባ ን ነገ  !

#ወይ_አዲስአበባ ን ነገ !
Photo: Social media

ጥበብና ባህል

#ወይ_አዲስአበባ ን ነገ  !

#ወይ_አዲስአበባ ን ነገ  !

ታዋቂ ብዕረኞችና አምደኞች አሻራቸውን ያኖሩባት፣  “ወይ አዲስ አበባ” መጽሔት የወርሐ-መጋቢት እትሟ የተለያዩ ጉዳዮችን አካትታ  ነገ በገበያ ላይ ትውላለች።

እነሆ … ተወዳጅዋ የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ዓለምፀሐይ ወዳጆ የ‘ቆይታ’ አምዳችን እንግዳ ናት።  ሰው፣ ሰው የሚሸትና ለዛ ያለው ቆይታ አድርጋለች – ከ “ወይ አዲስ አበባ” ጋር።  ከቀበና እስከ ዋሽንግተን የዘለቀው ሕይወቷ፣ ከፖለቲካ ፣ ከኪነ-ጥበብ፣ ከባህልና ከማኅበራዊ ጉዳዮች አኳያ ያለፈችባቸው እውነትና እምነቷም በቃለ ምልልሷ ተዳሷል።

አዲሱ ዘገየ “የትኛዋ ኢትዮጵያ?” ሲል ይጠይቃል – የታሪክ ይዘት ባለው መጣጥፉ። ምላሹን የምታገኙትም መጽሔቷን ከእጃችሁ ስታስገቡ ነው።

የሚዲያ ባለሙያው  ዮሴፍ ጥሩነህ “ምርጫና የማኅበራዊ ሚዲያ ፈተናዎች”ን በወጉ ቃኝቶት ታገኙታላችሁ።

ከሀገራችን ገናን ደራሲያን አንዱ የሆነው አዳም ረታም የልብወለድ፣ ኢ-ልብወለድ  መጻሕፍትና የፊልም  ምርጫዎቹን አጋርቶናል።

የሁለዜው አምደኛችን ኃይለጊዮርጊስ ማሞ  (ጲላጦስ)ም እንዲሁ   “የሸገር ልጅ ትዝብት”ን  ከሸገር ሆኖ ያስነብበናል።

ዶ/ር ዮናስ ባህረጥበብ ፣ የዓለማችን ጭንቅ ሆኖ የዘለቀው ኮቪድ 19  ዋርካዎቻችን በሆኑት አረጋውያን ላይ የጭካኔ እጁን እያሳረፈ መሆኑን የሚያስቃኝ መጣጥፉም በ“ወይ አዲስ አበባ” ላይ ይነበባል።

ተጓዡ ጋዜጠኛ ሔኖክ ስዩም በ“ግዕዝ” ዙሪያ የፃፈው መጣጥፉም “ወይ አዲስ አበባ” በዚህ እትሟ ካካተተችው መካከል ነው።

ሥዓሊ እሸቱ ጥሩነህ፣ ስለ ታላቁ የጥበብ ሰውና ፣ የሀገራችን ሥነ-ጥበብ ባለውለታ ስለሆኑት አለ ፈለገ ሰላም ታሪክና ሥራዎች በክፍል ሁለት ጽሑፋቸው ይነግሩናል። ሌሎች ያልጠቀስንላችሁንም በብዙ ደግሳ ትጠብቃችኋለች።

“ወይ አዲስ አበባ”ን ያንብቡ በ“ወይ

 

Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top