Connect with us

የኢትዮ-ኤርትራ ህዝቦች ለዘመናት የቆየ የወድማማችነት ግንኙነት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ለአመታት ተዘግቶ የቆየውን የኢኮኖሚግንኙነት ለማነቃቃት ተስማሙ

የኢትዮ- ኤርትራ ህዝቦች ለዘመናት የቆየ የወድማማችነት ግንኙነት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ለአመታት ተዘግቶ የቆየውን የኢኮኖሚ ግንኙነት ለማነቃቃት ተስማሙ
Photo: Social media

ዜና

የኢትዮ-ኤርትራ ህዝቦች ለዘመናት የቆየ የወድማማችነት ግንኙነት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ለአመታት ተዘግቶ የቆየውን የኢኮኖሚግንኙነት ለማነቃቃት ተስማሙ

የኢትዮ- ኤርትራ ህዝቦች ለዘመናት የቆየ የወድማማችነት ግንኙነት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ለአመታት ተዘግቶ የቆየውን የኢኮኖሚ ግንኙነት ለማነቃቃት ተስማሙ

(ዶ/ር አብርሃም በላይ~ የልዑካን ቡድኑ አባል)

ከሁለት አሰርት አመታት በፊት በኢትዮጰያና በኤርትራ መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ደም አፋሳሽና አውዳሚ ጦርነት ከሁለት አመታት በፊት የለወጠ የሰላም ስምምነት ተፈርሞ የነበረ ቢሆንም በአገራችን የውስጥ የፖለቲካ አደረጃጀት ስርአት ተገንነት የህወሀት አጥፊ ቡድን የሰላም ስምምነቱን ተጨባጭ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ኪሳራ ያስከተለ ጋሬጣ ሆኖ መቆየቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ይህ ቡድን በተለይም ከሰላም ስምምነቱ የትግራይ ህዝብ ሊያገኝ ይገባው የነበረው እፎይታ በኖረበት የሴራ ባህል ሊያከሽፍ ያለመታከት ከመስራቱም በላይ በመከላከያ ሀይላችን ላይ በፈፀመው ትንኮሳ መነሻነት የተወሰደውን የህግ የበላይነትን የማስከበር ዘመቻ ቀጠናዊ ይዘት ለማስያዝ ያልተሳካ ሙከራን አድርጓል።

ይህ የክህደት ተግባር በአገር ሉአላዊነት የማስከበር ወሳኝ አቅም ላይ በፈጠረው ጫና አገራችን በትግራይ ክልል ከኤርትራ ጋር በምትዋሰንባቸው አንዳንድ አካባቢዎች የኤርትራ ጦር መግባቱ ታውቆ  አፋጣኝ ማስተካከያዎች በሰላማዊ አግባብ የመፈፀም ተልእኮን እና አጠቃላይ የሁለቱ  አገራትን የማህበራዊ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር ላይ በዋነኛነት ያለመ ጉብኝት በክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ የተመራ የልኡካን ቡድን  የሁለት ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት በአስመራ አድርጓል።

ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ ከኤርትራው ፕረዚደንት ኢሳያስ ጋር ባደረጉት ውይይት በዋነኝነት ኤርትራ ከኢትዮጰያ ጋር በድንበር በምትዋሰንባቸው  በትግራይ ክልል ቦታዎች የሚገኙ ወታደሮችዋን በፍጥነት እንድታስወጣና ቦታዎቹ በኢፌዲሪ የመከላከያ ሀይሎች እንዲጠበቁ ከስምምነት የተደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ የቀጠናዊ ሰላም ጉዳይ ላይ ሀገራቱ ያላቸውን  አቋም በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።

የኢትዮ ኤርትራ ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በተለይም በአገራችን በትግራይና ሌሎች አዋሳኝ  ቦታዎች ለአመታት የቆየው ጠንካራ የህዝቦች  መስተጋብር ለዘላቂ የጋራ ሰላምና እድገት ዋስትናና አቅም መሆኑን ያስታወሰው ምክክር ትብብሩን በኢኮኖሚያዊ መስኩ በፍጥነት ለማሳደግ በሚያግዙ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ዝግጅቶች ሒደት ላይም ወሳኝ ምክክር አድርገዋል። 

በዚህም መሰረት በኢነርጂ ዘርፍ ልማት፣ ኤሌክትሪክ ሀይል መስመር ግንባታና አቅርቦት በሎጂስቲክስ ኮሪዶር ልማት ስራዎች በትብብር ለመስራት በሚቻልበት እድል ዙርያ ምክክር የተደረገ ሲሆን አገራቱ በከፍተኛ አስፈፃሚዎች የሚመሩ የትግበራ ቡድኖችን በማደራጀት ወደ ስራ ለመግባትም ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top