Connect with us

በሰባት ቀናት ብቻ ከ53 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዘ

በሰባት ቀናት ብቻ ከ53 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዘ
የገቢዎች ሚኒስቴር

ወንጀል ነክ

በሰባት ቀናት ብቻ ከ53 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዘ

በሰባት ቀናት ብቻ ከ53 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዘ

ከመጋቢት 7/2013 ዓ.ም እስከ መጋቢት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ግምታዊ ዋጋቸው 53 ሚሊዮን 027 ሺ 995 ብር ከ73 ሳንቲም የሆኑ የኮንትሮባድ እቃዎችን ለመያዝ ተችሏል፡፡  

የኮንትሮባድ እቃዎቹ በህገወጥ መንገድ ከሃገር ሊወጡ ሲሉ እና ወደሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ናቸው፡፡ ከተያዙት ውስጥ አብዛኛውን የሚሸፍኑት ወደሀገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙት የኮንትሮባንድ እቅዎች ሲሆኑ ግምታዊ ዋጋቸውም 51ሚሊዮን 370ሺ 705ብር ከ73 ሳንቲም ነው፡፡ ከሀገራችን ሊወጡ ሲሉ የተያዙት ደግሞ የ1ሚሊዮን 657ሺ 290 ብር ግምታዊ ዋጋ አላቸው፡፡

ከኮንትሮባንድ እቃዎቹ መካከልም የተለያዩ አልባሳት፣ ምግብ ነክ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሲጋራ፣ ኮስሞቲክስ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ ጫማ፣ መድሃኒት፣ መለዋወጫና ልዩ ልዩ አደንዛዥ ዕፆች እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ሀዋሳ፣ ጅጅጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሞያሌ፣ ባህርዳር፣ ጋላፊ፣ አ/አ ቃሊቲ፣ ጅማ፣ አዳማ፣ አዋሽ፣ ኮምቦልቻ እና አሶሳ የኮንትሮባንድ እቃዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉባቸው የጉምሩክ ቅርንጫፎች ናቸው፡፡

እነዚህን የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ለማዋል አስተዋፅኦ ላበረከቱ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች :የፀጥታ አካላትና የህብረተሰብ ክፍሎች የገቢዎች ሚኒስቴር ምስጋናውን ያቀርባል።

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top