Connect with us

በሀሰተኛ ሰነድ የውሎ አበል የወሰደው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በሀሰተኛ ሰነድ የውሎ አበል የወሰደው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

ወንጀል ነክ

በሀሰተኛ ሰነድ የውሎ አበል የወሰደው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በሀሰተኛ ሰነድ የውሎ አበል የወሰደው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በ2007ዓ.ም የወጣውን የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 23/3/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ መንግስታዊ መስሎ በተሰራ ሀሰተኛ ሰነድ የመገልገል ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡ 

ዘሪሁን ጋሻው የተባለ የ38 እድሜ ያለዉ ተከሳሽ የሌላውን ሰው መብት ወይም ጥቅም ለመጉዳት፤ ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ተገቢ ያልሆነ መብት ወይም ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ ህዳር 03 ቀን 2013ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ክልል ልዩ ቦታው ካዛንችስ ጁፒተር ሆቴል 9ኛ ፎቅ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በዓል ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ እራሱን ከድሬደዋ አስተዳደር እንደተወከለ በማስመሰል በስልጠናው ላይ ይካፈላል፡፡

በመቀጠልም በወቅቱ ለሰልጣኞቹ የተዘጋጀውን የትራንስፖርትና የውሎ አበል በመክፈል ላይ ለነበረው ሰራተኛ ተከሳሽ ከድሬደዋ አስተዳደር በቁጥር 1713/DD/H በቀን 06/03/13DD ተፅፎ የተሰጠ የሚል ሀሰተኛ የተሳታፊነት ማሳወቂያ ደብዳቤ በማቅረብ የውሎ አበል 1,448 (አንድ ሺህ አራት መቶ አርባ ስምንት ብር) እንዲሁም የትራንስፖርት 3,304 (ሶስት ሺህ ሶስት መቶ አራት ብር) በጠቅላላ 4,752 (አራት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ ሁለት ብር የወሰደ በመሆኑ በፈፀመው መንግስታዊ መስሎ በተሰራ ሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል መከሰሱን በአቃቢ ህግ የቀረበበት የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡

ክሱ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ 2ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት በእማኝነት የቀረበውን የምስክሮች ቃልና ማስረጃ መርምሮ ተከሳሽ ራሱን እንዲከላከል ቢያዝም የቀረበበትን ክስ ማስተባበል ባለመቻሉ የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዘሪሁን ጋሻው በ1 አመት ከ2 ወር ቀላል እስራትና በ2,000 (ሁለት ሺህ ብር) የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

 

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top