Connect with us

የማይካድራው ጭፍጨፋ በዓለም ከተከሰቱ 10 አስከፊ የሽብር ጥቃቶች አንዱ ሆኖ ተመዘገበ

የማይካድራው ጭፍጨፋ በዓለም ከተከሰቱ 10 አስከፊ የሽብር ጥቃቶች አንዱ ሆኖ ተመዘገበ
የፌዴራል ፖሊስ

ወንጀል ነክ

የማይካድራው ጭፍጨፋ በዓለም ከተከሰቱ 10 አስከፊ የሽብር ጥቃቶች አንዱ ሆኖ ተመዘገበ

የማይካድራው ጭፍጨፋ በዓለም ከተከሰቱ 10 አስከፊ የሽብር ጥቃቶች አንዱ ሆኖ ተመዘገበ

ጁንታው ባሰማራቸው ሳምሪ በተሰኙ ፀረ-ሰላም ሃይሎች ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ ቦኮሀራም ናይጄሪያ ላይ በተመሳሳይ ወር ከፈፀመው የሽብር ወንጀል በመቅደም በርካታ ንፁሃን ዜጎች የተገደሉበት ወንጀል ሆኖ መመዝገቡን አለም አቀፉ የፖሊስ ትብብር ተቋም ኢንተርፖል አስታወቀ።

በፈረንጆቹ የዘመን አቆጣጠር በወርሃ ህዳር 2020 ዓ.ም በመላው ዓለም የተፈፀሙ 10 አስከፊ  የሽብር ጥቃቶችን አስመልክቶ አለም አቀፉ የፖሊስ ትብብር ተቋም ኢንተርፖል ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በጁንታው ፀረ-ሰላም ሃይሎች ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ግድያ ቦኮሀራምና ሌሎች የሽብር ቡድኖች በተለያዩ ሀገራት ከፈፀሟቸው አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች በመብለጥ በርካታ ንፁሃን ሰዎች ህይወታቸውን ያጡበት ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው፡፡

ጁንታው እኩይ ተልዕኮውን ለማሳካት አስታጥቆ ያሰማራቸው ሳምሪ የተሰኙ የሰላም ተፃራሪ ሃይሎች በማይካድራ በፈፀሙት ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ 600 ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን በኢንተርፖል የሽብር ወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሬት ያወጣው መረጃ ያሳያል።

ከሶስት ወራት በፊት በህዳር ወር ላይ ብቻ በተፈፀሙ የሽብር ወንጀሎች አፍሪካ ቀዳሚ ስፍራ ላይ መቀመጧን የጠቀሰው የኢንተርፖል መረጃ ንፁሃን ላይ ባነጣጠሩ የጅምላ ግድያ ወንጀሎች በርካታ ህይወት መቀጠፉን አስገንዝቧል። የሽብር ቡድኖቹ ከሰብዓዊ ፍጡር በማይጠበቅ መልኩ ጭካኔ የተሞላባቸውን የጅምላ ጭፍጨፋዎች መፈፃማቸው የተገለፀ ሲሆን ከአፍሪካ በመቀጠል ደቡባዊ የእስያ አካባቢና ምስራቃዊ የሜዲትራኒያን ቀጠና የዚህ ሽብር ወንጀል ሰለባ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ወርሃ ህዳር ላይ ብቻ በተፈፀሙና በርካቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸውን ባጡባቸው የሽብር ወንጀል ድርጊቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገው የኢንተርፖል መረጃ በኢትዮጵያ ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋና ናይጄሪያ ውስጥ ሜይጉዱሩ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ቦኮሃራም ያካሄደው ግድያ በሰብዓዊነት ላይ ከተፈፀሙ ከባድ የሽብር ወንጀሎች ቀዳሚ ተርታ ላይ መሰለፋቸውን ያሳያል። የተለያዩ ኢ-ሰብዓዊ ዓላማዎችን ይዘው የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች በንፁሃን ላይ የሚፈፅሟቸው ግድያዎች አሳሳቢ መሆናቸውም በመረጃው ተጠቅሷል።

ከሶስት ወራት በፊት የንፁሃንን ህይወት የቀጠፉ የሽብር ወንጀሎች ከተፈፀሙባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን፣ ናይጄሪያን፣ ሞዛምቢክን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን፣ ሶማሊያን፣ ቡርኪናፋሶንና ቻድን የያዘችውን አፍሪካን በግንባር ቀደምትነት  የጠቀሰው የኢንተርፖል መረጃ ከሌሎች የአለም ክፍሎች ደግሞ ከደቡብ እስያ አፍጋኒስታን፣ ከምስራቅ ሜዲትራኒያን ሶሪያን እንዲሁም ኢንዶኔዥያንና ኦስትሪያን አካቷል። 

የሽብር ቡድኖቹ በእነዚህ ሀገራት በፈፀሟቸው አሰቃቂ የጅምላ ግድያዎች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በህዳር ወር 2020 ዓ.ም ብቻ ወደ አንድ ሺ የሚጠጉ ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን ኢንተርፖል ያወጣው መረጃ ይጠቁማል።

ኢንተርፖል ያሰባሰበው የመረጃው ግኝት እንደሚያሳየው መንግስታዊ ባልሆኑ ታጣቂ ቡድኖች ከተፈፀሙ ጥቃቶች አራቱና በከፍተኛ ሁኔታ የንፁሃንን ህይወት የቀጠፉ የሽብርተኝነት ወንጀሎች በአፍሪካ፣ በደቡብ እስያ (በዋናነት በአፍጋኒስታን) በባህረ ሰላጤ አካባቢ ሀገራት በዋነኝነት በየመንና በምስራቅ ሚዲትራኒያን (በሶሪያ) የተፈፀሙ መሆናቸውንም ያመላከተ ሲሆን በኢትዮጵያ ሳምሪ የተሰኙ የጁንታው ሃይሎች ማይካድራ ላይ የፈፀሙትና በናይጄሪያ በቦኮሀራም የተፈፀሙት ኢ-ሰብአዊ ጭፍጨፋዎች ከሁሉም የከፋ እልቂት የተመዘገበባቸው የሽብር ወንጀሎች መሆናቸውን ገልጿል፡፡(የፌዴራል ፖሊስ)

 

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top