Connect with us

በጋምቤላ 65 የወንጀል ተጠርጣሪዎች ተያዙ

በጋምቤላ 65 የወንጀል ተጠርጣሪዎች ተያዙ
Ethiopian News Agency

ወንጀል ነክ

በጋምቤላ 65 የወንጀል ተጠርጣሪዎች ተያዙ

በጋምቤላ 65 የወንጀል ተጠርጣሪዎች ተያዙ

በጋምቤላ ክልል ከጽንፈኛው ህወሓትና ኦነግ ሸኔ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 65 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር እንዳዋለ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ህዝብ ከጸጥታ አካላት ጎን በመሰለፍ የጽንፈኛው ቡድንና የሌሎች ቅጥረኞችን ሴራ በማምከን ረገድ የበኩሉን ሚና እንዲወጣም ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር ኡማን ኡጋላ እንዳሉት፤ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች በክልሉ ህዝብና ተቋማት ላይ ጉዳት ለማድረስ ሲያሴሩ የነበሩ ናቸው።

ህወሐት ከሌሎች የሽብር ቡድኖች ጋር በመቀናጀት ቅጥረኞችን በማሰማራት በንጹሃን ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ለማድረስ አቅዶ ሲሰራ እንደነበር ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ የፖሊስ ኮሚሽኑ የጥፋት ቡድኑን ሴራ በመገንዘብ ከሌሎች የፌዴራል የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረገው ክትትል እስከ ትናንት ባለው ጊዜ 65 ተጠርጣሪዎችን በህግ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ነው የገለጹት።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች በጋምቤላ ከተማና በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች የብሔር ግጭት በማስነሳት በሰው ህይወትና በተቋማት ላይ ጉዳት ለማድረስ እንደሚሰሩ በመጠርጠራቸው እንደሆነም ተናግረዋል።

የጽንፈኛው ህወሓት ቡደን ካፈነገጠበት ጊዜ ጀምሮ በጸጥታ አካላትና በክልሉ የፖለቲካ አመራር ጭምር በተከናወኑት ስራዎች የክልሉ ሰላም ከሌሎች አካባቢዎች በተሻለ ሁኔታ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

(ኢዜአ)

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top