Connect with us

በሐረሪ ክልል ለጥፋት ሲዘጋጁ የነበሩ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በሐረሪ ክልል ለጥፋት ሲዘጋጁ የነበሩ 17 ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች ጋር በቁጥጥር ሥር ዋሉ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ወንጀል ነክ

በሐረሪ ክልል ለጥፋት ሲዘጋጁ የነበሩ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በሐረሪ ክልል ለጥፋት ሲዘጋጁ የነበሩ 17 ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና  ሌሎች ቁሳቁሶች ጋር በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በሐረሪ ክልል ሐኪም ወረዳ ለጥፋት ዓላማ ሲዘጋጁ የነበሩ 17 ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እና ሌሎች ቁሳቁሶች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ምክትል ኮማንደር ናስር ከድር እንደገለጹት፣ በወረዳው ጥፋት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።

የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣት ከጸጥታ ሃይሉ፣ ከወረዳው መስተዳድር፣ ከንዑስ ቀበሌ አመራር፣ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን በአስራ አምስቱም ተጠርጣሪዎች መኖርያ ቤት በተደረገው ፍተሻ በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተይዘዋል።

የጦር ሜዳ መነጽር፣ የራዲዮ መገናኛ፣ ፎቶ ካሜራ፣ የጦር መሳርያ መያዣ ቁሳቁሶች፣ 20 የሚደርሱ ሲምካርዶች፣ የጦር ሜዳ የመጀመርያ ህክምና መስጪያ ቁሳቁሶች ከተጠርጣሪዎቹ የሽብር መልዕክተኞች የተያዙ ናቸው።

በተጨማሪም የተለያዩ መታወቂያዎች፣ የባንክ ቤት ቼክና ደብተር፣ ላፕቶፖች፣ የጸረ ሽምቅ ውጊያ ማስተማሪያ መጽሃፎችና ሌሎች ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር ናስር ተናግረዋል።

እንዲሁም ሌላ አንድ ግለሰብ በተለያዩ ስሞች 7 መታወቂያ ይዞ ሲንቀሳቀስ እንደተገኘ ጠቁመው ከግለሰቡ ጋር ግንኙነት ያለው ሌላ ተጠርጣሪ ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ግለሰቦቹ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱና ይሄንንም ለሽብር ተግባር ማስፈጸሚያ ሊጠቀሙበት እየሞከሩ መሆናቸውንም አዛዡ ጠቁመዋል።

ባጠቃላይ በወረዳው ባለፉት 15 ቀናት በተካሄደው የኦፕሬሽን ስራ 17 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ተናግረዋል::

ህብረተሰቡ በአካባቢው የጸጉረ ልውጦችን የወንጀል እንቅስቃሴ ሲመለከት በአካባቢው ለሚገኙ የጸጥታ ሃይል ጥቆማ በመስጠት ሃላፊነቱን እንዲወጣ ምክትል ኮማንደር ናስር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል። (EBC)

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top