Connect with us

በጅማ ከተማ ባለፉት ሁለት ቀናት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጅማ ከተማ ባለፉት ሁለት ቀናት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ወንጀል ነክ

በጅማ ከተማ ባለፉት ሁለት ቀናት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጅማ ከተማ ባለፉት ሁለት ቀናት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጅማ ከተማ ባለፉት ሁለት ቀናት በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ በህዝብ ላይ ጥቃት ለማድረስ የተዘጋጁ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት 8 ሽጉጦች፣ 7 ክላሾች፣ ከ130 በላይ የተለያዩ ጥይቶች፣ የጦር ሜዳ መነፅር እና የተለያዩ አገራት ፓስፖርቶች ከያዙ 31 ተጠርጣሪዎች ናቸው።

በህዝቦች መካከል ልዩነት በመፍጠር ኢትዮጵያን ወደ ብጥብጥ የሚመሩ አካላትን በፅኑ እንደሚያወግዙም የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በወቅታዊ የጅማ ከተማና አካባቢው ሰላም ላይ ውይይት እያደረጉ የሚገኙት ነዋሪዎቹ የአካባቢውን ሰላም ነቅቶ ለመጠበቅ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

በከሀዲው የህወኃት ቡድን በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊታችን ላይ የተሰነዘረው ጥቃት አሳዛኝ፣ አሳፋሪም ነው ያሉት ነዋሪዎቹ ቡድኑ ድባቅ እስኪመታ ድረስ ከአገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በፅናት እንደሚቆሙም ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል።(EBC)

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top