Connect with us

አደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ተያዙ

አደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ተያዙ
የፌደራል ፖሊስ

ወንጀል ነክ

አደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ተያዙ

አደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ተያዙ

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ምክትል ዳይሬክቶሬት በአለም አቀፍ በአደገኛ እፅ አዘዋዋሪነት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አዋለ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ምክትት ዳይሬክቶሬት አባላት በትላንትናው እለት በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ባደረጉት ፍተሻ መነሻቸውን ላቲን አሜሪካ፣ ሳኦፖሎ ከተማ፣ መዳረሻቸውን ደግሞ የተለያዩ ሀገራት ለማድረግ በአውሮፕላን ሲጓዙ የነበሩት ተጠርጣሪዎችን  እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን  በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር  ኦፕሬሽን ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር መንግስትአብ በየነ ገልጸዋል፡፡

የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ ምንም እንኳን አደንዛዥ ዕፁን በውስጣዊና ውጫዊ የሻንጣ አካል በመደበቅ፣በሆዳቸው በመዋጥ እንዲሁም የጡት መያዣና የተለያዩ የማዘዋወሪያ ዘዴዎችን ተጠቅመው ለማሳለፍ ሙከራ ቢያደርጉም የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ምክትት ዳይሬክቶሬት አባላት ባደረጉት ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ምክትት ዳይሬክቶሬት በሀገር ውስጥ የሚያበቅሉ፣የሚያዘዋውሩና የሚጠቀሙትን በመከታተል በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ እንደሚያቀርቧቸው የገለጹት ምክትል ዳይሬክተሩ በትላንትናው እለትም በጥናት ላይ የተመሰረተ ክትትል በማድረግ 13 ናይጄሪያውያንና አንዲት ብራዝላዊትን ጨምሮ በአጠቃላይ 14 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ጠቁመዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከ14 ኪ.ግ በላይ የሚመዝን ኮኬይን የተሰኘ አደገኛ ዕፅ ይዘው የተገኙ ሲሆን አደገኛ ዕፁ በላቲን አሜሪካ አካባቢ የሚመረትና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚዘዋወር መሆኑንም ምክትል ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ኮማንደር መንግስትአብ አያይዘውም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ምክትል ዳይሬክቶሬት አባላት የወትሮ ዝግጁነታቸውን በማጠናከርና ከግዜ ወደ ግዜ ሙያዊ ክህሎታቸውን  በማዳበር እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ወንጀሉን ከመከላከል አንጻር ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በሶስት ወር ውስጥ ብቻ ወደ 24 የወንጀሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 39 ኪ.ግ ኮኬይንና 36 ኪ.ግ የሚመዝን ካናቢስ የተባለ አደገኛ እፅ መያዛቸው ተገልጿል፡፡

የአደገኛ እፅ ዝውውር በሀገር ላይ የሚያደርሰው ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለትካዊው ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑ  ይህንን ህገ ወጥ ተግባር ለመከላከል የጸጥታ አካላት ለሚያደርጉት ጥረት ህብረተሰቡ ድጋፉን አጠናክረው መቀጠል እንዳለበትም ኮማንደር መንግስትአብ በየነ ጥሪ አቅርበዋል፡፡(የፌደራል ፖሊስ)

 

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top