Connect with us

የ100 የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ሀብት እንዲጣራ ለፌዴራል ፖሊስ ሊተላለፍ ነው ተባለ

ሀብትና ንብረታቸውን ያላስመዘገቡ 100 የፌዴራልና የአ.አ ከተማ አስተዳደር የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ስም ዝርዝር ለፌዴራል ፖሊስ ሊተላለፍ ነው
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

የ100 የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ሀብት እንዲጣራ ለፌዴራል ፖሊስ ሊተላለፍ ነው ተባለ

ሀብትና ንብረታቸውን ያላስመዘገቡ 100 የፌዴራልና የአ.አ  ከተማ አስተዳደር የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ስም ዝርዝር  ለፌዴራል ፖሊስ ሊተላለፍ ነው

የፌዴራል ሥነምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ሀብትና ንብረታቸውን ያላስመዘገቡ 100 የፌዴራልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት የስራ ሀላፊዎች አስፈላጊውን የህግ ማጣራት እንዲደረግባቸው ስም ዝርዝርቸውን ለፌዴራል ፖሊስ እንደሚያስተላልፍ አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ ዛሬ ለኢዜአ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች 1ሺህ ብር እየተቀጡ ሀብትና ንብርታቸውን እንዲያስመዘግቡ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ እስከ ዛሬ 11 ሰዓት ከ30 ድረስ ብቻ ነበር።

በተቀመጠው የጊዜ ገደብ  ሀብትና ንብረታችውን ያላስመዘገቡ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች የህግ ማጣራት እንዲደረግባቸው ለፌዴራል ፖሊስ ስም ዝርዝራቸው ይተላለፋል ነው ያሉት።

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም ኮሚሽኑ ከተሰጡት ተልዕኮዎች አንዱ በፌዴራል፣  አዲስ አበባና ድረዳዋ ከተማ አስተዳደሮች  የመንግስት ተመራጮችና ተሿሚዎች ሀብትና ንብረታቸውን እንዲያስመዘግቡና እንዲያሳውቁ ማድረግ ነው።

በዚህም በፌዴራልና በአዲስ አበባ የሚገኙ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ሀብትና ንብረታቸውን  እንዲያስመዘግቡ  መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ  በተለያዩ አማራጮች ጥሪ ቀርቦ እንደነበር በመግለጫቸው ተናግረዋል።

የተሰጠውን የጊዜ ገደብ ተጠቅመው ሀብት ንብረታቸውን ያላስመዘገቡ 180 የሚሆኑ በፌደራልና አዲስ አበባ የሚገኙ የስራ ሀላፊዎች የተደረገውን ጥሪ ተቀብለው ባለማስመዝገባቸው  እስከ ዛሬ ድረስ  1 ሺህ ብር የቅጣት መቀጮ ተጥሎባቸው ሀብት ንብረታቸውን እንዲያስመዘግቡ ተደርጎ ነበር።

ከላይ ከተጠቀሱት 180 የስራ ሀላፊዎች ውስጥ 80 የሚሆኑ የስራ ሀላፊዎች እየተቀጡ ማስመዝገባቸውን ጠቁመዋል።

ቀሪዎች 100 የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ግን በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ሀብት ንብረታቸውን ባለማስዘግባቸው አስፈላጊው የህግ ማጣራት እንዲደረግባቸው ለፌዴራል ፖሊስ ስም ዝርዝራቸው እንደሚተላለፍ ገልጸው፤ በቀሩት ሰዓታት ውስጥ ሀብትና ንብረታቸውን እንዲያስመዘግቡም ጥሪ  አቅርበዋል።

(ኢዜአ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top