Connect with us

የፖሊስ አባል ለስራ በታጠቀው መሳሪያ የአራት ሰዎችን ህይወት አጠፋ

የፖሊስ አባል ለስራ በታጠቀው መሳሪያ የአራት ሰዎችን ህይወት አጠፋ
Photo: Social Media

ወንጀል ነክ

የፖሊስ አባል ለስራ በታጠቀው መሳሪያ የአራት ሰዎችን ህይወት አጠፋ

በአዲስ አበባ አንድ የፖሊስ አባል ለስራ በታጠቀው መሳሪያ የአራት ሰዎችን ህይወት መቅጠፉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ወንጀሉን በመፈፀም የተጠርጣረው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑም ታውቋል።
የፖሊስ አባሉ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው መስከረም 1 ቀን 2013 ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ30 ገደማ በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተለመዶ ጨርጨር ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ተጠርጣሪው ከትዳር አጋሩ ጋር በነበረው አለመግባባት በእለቱ አራት ቤተሰቦቿን ተኩሶ መግደሉ ታውቋል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጀይላን አብዲ ለኢዜአ እንደገለጹት የፖሊስ አባሉ ከትዳር አጋሩ ጋር በፈጠረው ቅራኔ ተነሳስቶ 4 ቤተሰቦቿን ገድሏል።

ከትዳር አጋሩ ጋር ላለፉት ሁለት ዓመታት አብረው ይኖሩ የነበረ ቢሆንም ሰሞኑን በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ወደ ቤተሰቦቿ ቤት መሄዷ ተገልጿል።

ፖሊሱ ወደ ሚስቱ ቤቷ እንዲትመለስና አብረው እንዲኖሩ ቢጠይቃትም ፈቃደኛ ባለመሆኗ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት በማቅናት የቤተሰቧ አባል የሆኑትን አራት ሰዎች ተኩሶ መግደሉን አቶ ጀይላን ገልጸዋል።

የወንጀሉ ተጠርጣሪ የሚስቱን እናት፣ የሚስቱን የእንጀራ አባት፣ የሚስቱን እህት ባል እንዲሁም አንድት የቤት ሰራተኛ ተኩሶ መግደሉ ታውቋል።

የፖሊስ አባሉ በፈጸመው ድርጊት በእጂጉ ማዘናቸውን የገለጹት ሃላፊው ጉዳዩ ተጣርቶ በህግ ተገቢው ውሳኔ ይሰጣልም ብለዋል።
የተፈጸመው ድርጊት ተቀባይነት የሌለውና አሳዛኝ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም ለሟቿች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።
አሁን ላይ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑንም አቶ ጀይላን ገልጸዋል።

የኮሚሽኑ አባላት ራሳቸውን ለመስዋእትነት በማዘጋጀት አገራቸውንና ህዝባቸውን እያገለሉ መሆኑን የገለጹት፤ ሃላፊው ተጠርጣሪው በፈፀመው እኩይ ተግባር ሁሉም ማዘናቸውን ጠቅሰዋል።

በኮሚሽኑ ስም ለሟች ቤተሰቦችና ለአካበቢው ማህበረሰብ መፅናናትን ተመኝተዋል።

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top