Connect with us

በአዲስአበባ ከመሬት ጋር የተይያዙ አገልግሎቶች ላልተወሰነ ጊዜ ታገዱ

በአዲስአበባ ከመሬት ጋር የተይያዙ አገልግሎቶች ላልተወሰነ ጊዜ ታገዱ
A new social housing project on the edge of Addis Ababa. Photograph: Charlie Rosse

ህግና ስርዓት

በአዲስአበባ ከመሬት ጋር የተይያዙ አገልግሎቶች ላልተወሰነ ጊዜ ታገዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህገወጥ መሬት ወረራ ጋር በተያያዘ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እስኪጣሩ እና አሰራሮች እስኪስተካከሉ ከመሬት ጋር ተያይዞ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ላልተወሰነ ጊዜ አቆመ።

በከተማ አስተዳደሩ የምክትል ከንቲባ ፅህፈት ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊ የሆኑት አቶ ደረጄ ካሳ ለካፒታል ጋዜጣ እንደገለፁት የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ፣ የስም ማዞር፣ የኮንስትራክሽን ስራዎች እና የመሳሰሉትን የመሬት አስተዳደር የሚሰጣቸው አገልግሎቶች መረጃዎች ተጣርተው አሰራሮች እስኪስተካከሉ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ እንደቆሙ ገልፀዋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ አደረኩት ባለው ጥናት በከተማዋ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ህገወጥ የመሬት ወረራ መኖሩን እንደገለፀ የሚታወስ ነው፡፡ እንደ ጥናቱ ገለፃ በህገወጥ መሬት ወረራ እና ያላግባብ የኮንዶሚኒየም ቤቶች እደላ ላይ በስልጣን ላይ ካሉ አመራሮች ጀምሮ ተሳታፊ እንደሆኑ ሲገልፅ በተጨማሪም በብሄር ተለይቶ ድርጊቶች እንደሚፈፀሙ ያትታል፡፡

የቀድሞ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ሲሰጡ በህገ ወጥ መንገድ የኮንዶሚኒየም እደላ ተብሎ የተጠቀሰው 20 ሺ ለሚሆኑ ለቤት ግንባታ ከእርሻ ቦታቸው ተፈናቃይ ለሆኑ አርሶ አደሮች የተሰጡ እንደሆኑ እና አነሱም በአጠቃላይ ተነሺ ከሆኑት 67 ሺ አርሶ አደሮች በባሰ ሁኔታ ይገኛሉ ተብለው የተመረጡ እንደሆኑና ይሄም ከአንድ አመት ተኩል በፊት የተከናወነ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በቅርቡ የቀድሞው ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ በከተማዋ ውስጥ እየተለመደ የመጣውን ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመቆጣጠር የመሬት ምዝገባና ኦዲት አንዲሁም ለአርሶ አደሮች የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ እስከ ጥቅምት 2013 ድረስ እንዲሰጥ ለሁሉም ክፍለ ከተማ አስተዳደሮች ትእዛዝ ሰጥተው ነበር፡፡

(Capital )

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top