Connect with us

ኢዜማ መግለጫ እንዳይሰጥ በፖሊስ ተከለከለ

ኢዜማ መግለጫ እንዳይሰጥ በፖሊስ ተከለከለ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ኢዜማ መግለጫ እንዳይሰጥ በፖሊስ ተከለከለ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሔዱ የመሬት ወረራዎችን እና ኢ-ፍትሀዊ የሆነ የመኖሪያ ቤቶችን ክፍፍል በሚመለከት በራስ ሆቴል ሊሰጥ የነበረው መግለጫ በፖሊስ ተበትኗል።

የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ናትናኤል ፈለቀ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ከቀናት በፊት ስለ ስለ ስብሰባው ለሰላም ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም እንደሚደረገው ሁሉ በደብዳቤ ያሳወቁ ቢሆንም ዛሬ ነሐሴ 22/2012 በራስ ሆቴል ሊሰጥ ነበረው መግለጫ ግን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስለ መግለቻው መረጃ የለኝም በሚል መግለጫው እንዳይካሔድ መከልከሉ ታውቋል ሲል አዲስ ማለዳ ዘግቧል።

የኢዜማ ህዝብ ግንኙነት ቋሚ ሰብሳቢ ናትናኤል ፈለቀ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “ዛሬ ሊካሄድ የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋዜጣዊ መግለጫውን መስጠት እንደማንችል አሳውቆናል። የፈሩት ምን እንደሆነ እናውቃለን።

የጋዜጣዊ መግለጫውን ይዘት ነው የፈሩት። ህግ ማስከበር ጉዳያቸው ቢሆን ኖሮ ዛሬ የምንናገረውን ነገር ማስቆም ግዴታቸው ነበር። እሱን ማድረግ ሳይችሉ ጋዜጣዊ መግለጫ ስናደርግ ነው የከለከሉን፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ነው እንዲመሰረት የምንፈልገው፣ እንደዚህ አይነት ስራዎች ናቸው እንቅፋት እንደሆነ የምናምነው።

መግለጫውን በተለያየ መንገድ ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል። ለዛሬ ግን ስለመጣችሁ እናመሰግናለን” በማለት በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞችን አሰናብተዋል።

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top