Connect with us

በብልፅግና ፓርቲ እና በህወሓት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባትና መካረር በተመለከተ

ኘሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በብልፅግና ፓርቲ እና በህወሓት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባትና መካረር በተመለከተ:-
Photo: Social Media

ነፃ ሃሳብ

በብልፅግና ፓርቲ እና በህወሓት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባትና መካረር በተመለከተ

ኘሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በብልፅግና ፓርቲ እና በህወሓት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባትና መካረር በተመለከተ:-

***
“…የአንድ ግንባር አባል ሆነው ይህችን አገር ለበርካታ ዓመታት የመሩ ሰዎች ናቸው ዛሬ መግባባት አቅቷቸው የበደሉትን ሕዝብ መካስ ሲገባቸው እንደገና እየበደሉት ያሉት፡፡ አመራሩ ከሌብነት መጽዳት ሲያቅተውና የጠራ ፖሊሲና ስትራቴጂ ነድፎ አገር መምራት ሲሳነው የሕዝቦችን ስሜት እየኮረኮረ ወደ ጦርነት ለመማገድ ሲፍጨረጨር እየታዝብ ነው፡፡ ይህች አገር ከበቂ በላይ ደምታለች፣ ተጎድታለች፡፡ አሁን የሚያስፈልገን ሰላምና መረጋጋት ነው፡፡ ሕዝቡ እየጠየቀ ያለው ልማት ነው፡፡ በሰላም ወጥቶ መግባትና በልቶ ማደር ነው የሚፈልገው፡፡

በፖለቲከኞች በኩል የሚታየው ደግሞ ከዚህ ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ነገር ነው፡፡ ብሔራዊ መግባባት ፈጥሮ ፊትን ወደ ልማት ማዞር ሲገባ በአገራችን እያየን ያለነው ግን ወደኋላ የመሄድ ነገር ነው፡፡ እርግጥ ሁሉም ስለ ሰላም ያወራሉ፤ ፍትሕ፣ ዴሞክራሲና ልማት ይላሉ፡፡ ተግባራቸው ግን ከሚናገሩት ተቃራኒ ነው፡፡

በሁለቱ ኀይሎች መሀከል ያለውን መካረር በተመለከተ፣ እኔ በግሌ በፍፁም ወደ ኀይል እርምጃ ውስጥ መገባት የለበትም ነው የምለው፡፡ እንደምናየውና እንደምንሰማው ከንዴትና ከብስጭት ተነስቶ በሁለቱም ወገን የማይባል ነገር የለም፡፡ በሁለቱም ወገን በሕገ መንግሥቱ እየተማለ ሕገ መንግሥቱን የሚጥሱ በርካታ ተግባራትን እያየን ነው፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊትም የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የትግራይ ክልል መንግሥት መሀል የመግለጫ ውርውሮችን ተመልክተናል፡፡ ምናልባት ሳሳም፣ ጠጠርም ያሉ እርምጃዎችን ወደፊት እናይ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አንዲትም ጥይት ለመተኮስ ወደሚያበቃ ሁኔታ ውስጥ መግባት የለብንም፡፡ አንዳንድ አርቆ ማሰብ የተሳናቸው አካላት ጦርነት እንዲጀመር ሊቀሰቅሱ ይችላሉ፡፡ እንደሱ ዓይነት አዝማሚያም ይታያል፡፡ ስለ አገርና ስለ ሕዝብ ዘላቂ ሰላም የሚጨነቁ ኢትየጵያዊያን ግን ይህን አይፈልጉትም፡፡

ሁላችንም እንደምንረዳው የመንግሥት አቅም ፈርጀ ብዙ ነው፡፡ በተለያየ መንገድ የአገሪቱን ሕግ የጣሰ አካል መልዕክት እንዲያገኝ ማድረግ አያቅተውም፡፡ ነገር ግን በየትኛውም መንገድ ጥይት ሳይጮህ ችግሮች መፈታት አለባቸው፡፡

ሁለቱን አካላት ለመሸምገል ከሰማይ የከበዱ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች መሃል ገብተው ክብደት የሰጣቸው አካል እኮ አልነበረም፡፡ ቀጣይ የሚመጣውን አሁን ላይ መገመት አዳጋች ነው፡፡ ሁኔታውን ግን በጥሞና ማየት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ፍትጊያ ውስጥ ማሰብ የሚችል እና አእምሮ ያለው ይነቃል ብዬ አስባለሁ፡፡ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው አሁን ባለው የሕወሓትና ብልጽግና መሪዎች ፍጥጫ እና ትግል የሚጠቀም ሕዝብ የለም፡፡ ሕወሓትም ቢሆን ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር በመፋጠጥ የሚያተርፈው ነገር የለም፡፡ (ምንጭ:-ሲራራ)

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top