Connect with us

መረጃ አዘል ጥያቄ!

መረጃ አዘል ጥያቄ!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

መረጃ አዘል ጥያቄ!

#መረጃ_አዘል_ጥያቄ!

የትምህርት ሚኒስቴር ከነሐሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ት/ቤቶች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ለ2013 የትምህርት ዘመን ምዝገባ እንዲያካሂዱ ሰሞኑን ፈቃዱን ሰጥቷል። በሌላ በኩል የትምህርት መጀመሪያ ጊዜ መቼ ነው የሚለው አለመወሰኑን ጠቁሟል።

ይኸ የሚኒስቴሩ ውሳኔ አነጋጋሪ ሆኗል። በወላጆች በኩል የኮሮና ወረርሽኝ በተስፋፋበት በዚህ ወቅት ምዝገባ ይደረግ የሚል ጥድፊያ ውስጥ የተገባው ማንን ለመጥቀም ነው? ትምህርት የሚጀመርበት ጊዜ ሲወሰን ምዝገባ ቢካሄድ ችግሩ ምንድነው በሚል ጥያቄ እየቀረበ ይገኛል።

ሌሎች ወገኖች ደግሞ የውሳኔውን ተገቢነት ከት/ቤቶች እና መምህራን ጥቅም አንፃር በማየት ትክክል ነው ይላሉ።
#ጥያቄ:- በዚህ ጉዳይ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድነው? ( በተለይ ወላጆች፣ መምህራን እና የትምህርት አካላት እንዲሳተፉ እናበረታታለን።)

ለጠቅላላ ግንዛቤ ያህል በአዲስአበባ የኮሮና ወረርሽኝ በተመለከተ ሰሞኑን ከተለቀቁ ዜናዎች አንዱ ከዚህ በታች ቀርቧል።
***

“በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር የ 58 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል”
.~ “በሰባት ቀናት ብቻ በከተማዋ 119 ሰዎች በኮቪድ ህይወታቸው አልፏል ” -ጤና ቢሮ
*******************************

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ሰባት ቀናት (ከነሃሴ 8-14) 4ሺህ 767 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል፡፡

በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከነሃሴ ወር መጀመርያ ተመዝግቦ ከነበረው 3016 አንጻር የ 1 ሺህ 751 ወይም የ 58 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የከተማዋ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

ይህም የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ያሳያል ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል ባለፉት ሰባት ቀናት በከተማዋ 119 ሰዎች በኮቪድ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡

በነሃሴ ወር መጀመርያ 93 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በዚህ ሳምንት 119 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡

24 በመቶ የሚሆነው የሞት መጠን የተመዘገበው በያዝነው ወር በሁለተኛ ሳምንት በነበሩት ሰባት ቀናት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህም ከባለፈው ሳምንት አንጻር የ 26 ሰዎች ህልፈት ወይም 28 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ቢሮው አስታውቋል (ኢኘድ)

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top