Connect with us

በትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ያልታዩት አደጋዎችና ስጋቶች

በትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ያልታዩት አደጋዎችና ስጋቶች
Photo: AP

ጤና

በትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ያልታዩት አደጋዎችና ስጋቶች

በትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ያልታዩት አደጋዎችና ስጋቶች
(ዶ/ር ቤቴል ደረጄ)
…ትምህርት ቤቶች ምዝገባ እንዲያካሂዱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ለምን መቸኮል አስፈለገን? በተለይ አዲስ አበባ ላይ? እስካሁን ባለው የወረርሽኙ ስርጭት ማዕከሏ ዋና ከተማችን ከመሆና አንጻር እንደ ህክምና ባለሙያ ብቻ ሳይሆን እንደ ወላጅም ይህ ውሳኔ አሳስቦኛል።
1) ወረርሽኙ በሀገራችን በብዛት እየጨመረ በመጣበት ሁኔታ መቼ እንደሚከፈት ባልታወቀው ትምህርት ቤት ”ተማሪዎችን መዝግቡ” ብሎ መፍቀድ ትምህርት ቤቶቹ ገንዘብ እንዲያገኙ ከማመቻቸት የተለየ ተልኮ ያለው አይመስለኝም።
2) በአፍሪካ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀመር የዓለም ጤና ድርጅት ቢያሳውቅም የእኛን ሀገር የትምህርት አሰጣጥ ሁኔታ ያገናዘበ እይታ እና ውሳኔ ይፈልጋል።
ለምሳሌ
በአንድ ክፍል ውስጥ የሚማሩት የተማሪዎች ብዛት
~ የመማሪያ ክፍሎቹ ብዛት፣ ንፅህናና የአየር ዝውውር
~ የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና መፀዳጃ ቤቶቻቸው
~ የመመገቢያ ቦታዎች፣ የመጫወቻ ቦታዎችና የሚገለገሉባቸው የትራንስፖርት አማራጮች ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከምንፈልገው በተፃራሪው ሆነው እናገኛቸዋለን።
3) ”ሕፃናትን በሽታው ብዙ አይጎዳቸውም” የሚል አስተያየት ሲነገር ሰምተናል። ብዙ ሕፃናት በከፍተኛ ሁኔታ ባይጎዱም በቫይረሱ አይያዙም ወይንም አያስተላልፉም ማለት ግን አይደለም። ስለዚህም የተጓዳኝ ህመም ያለባቸው ሕፃናት በኮቪድ-19 እጅጉን ሊጎዱ ሕይወታቸውም ሊያልፍ ይችልል።
ሌሎች ሕፃናት ደግሞ በበሽታው የከፋ ጉዳት ባይገጥማቸው እንኳን ለቤተሰብ አባሎቻቸውና ለመምህራኖቻቸው ቫይረሱን ሊያስተላልፋ ይችላሉ። እዚህ ላይ ቆም ብለን እንድናስብ የምፈልገው በባለሙያ እና በሕክምና ቁሳቁስእጥረት በከፋ ችግር ውስጥ ያሉትን የጤና ተቋሞቻችንን ነው። ብዙ የታመመ ሰው ባለን ቁጥር ለብዙ ሰው የሚበቃ አቅምም አቅርቦትም የለንም።
4) የ4 ዓመቱ ልጄን አሰብኩና እራሴን እንዲህ ስል ጠየቅሁ።
~ እንዴት አድርጌ ነው በማስክ የምልከው?
~ ሳይሰለች ለስንት ሰዓት ማስኩን አድርጎ ይቆይ ይሆ?
~ እንዴት አድርጎ ነው እርቀቱን ጠብቆ የሚጫወተው?~ አስተማሪዎቹ በቀን ስንት ግዜ እጁን እንዲያፀዳ ያግዙት ይሆን?… ጥያቄዎቹ ብዙ ናቸው።
5) የትምህርት ሚኒስቴር እነዚህን ሁኔታዎች ባገናዘበ መልኩ ትምህርት ቤቶችን በማገዝና በመቀናጀት የወላጆችን ሥጋት መቅረፍ ካልቻለ ለልጆቻችን የትምህርት ሁኔታ በቤት ውስጥ ማስጠናትን ጨምሮ ሌሎች አማራጮችን ለመፈለግ ልንገደድ እንችላለን። ለምሳሌ በአንዳንድ ሀገሮች እንደሚደረገው ልጆቻችንን በየቤታችን በማስተማር የሚኒስቴር መስሪያቤቱ ለዝውውር ብቁ የሚያረጋቸውን አሰራር እዲያቀርብልን መጠየቅ ሌላኛው አማራጭ ሊሆን ይችላል!!!!
ውሳኔዎቻችን ከአደጋ የፀዱ እንኳን ባይሆኑ አደጋውን እንቀንስ።

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top