Connect with us

ጃዋር መሐመድ በግል ሐኪም እንዲታከም ጥብቅ ትዕዛዝ ተሰጠ

ጃዋር መሐመድ በማለቱ በግል ሐኪም እንዲታከም ጥብቅ ትዕዛዝ ተሰጠ
Photo: Social Media

ወንጀል ነክ

ጃዋር መሐመድ በግል ሐኪም እንዲታከም ጥብቅ ትዕዛዝ ተሰጠ

ጃዋር መሐመድ <<በማላውቀው ሐኪም መነካት አልፈልግም>> በማለቱ በግል ሐኪም እንዲታከም ጥብቅ ትዕዛዝ ተሰጠ
– የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን መስማት ተጀመረ

አቶ ጃዋር መሐመድ ከአራት ቀን በፊት ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደታመመ ለፍርድ ቤት በማስረዳት የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ሳይሰሙ ለዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. በተቀጠረው መሠረት የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች መሰማት ጀመሩ።

ምስክሮች ከመሰማታቸው በፊት ፍርድ ቤቱ ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. የሰጣቸው ትዕዛዞች መፈጸም አለመፈጸማቸውን አረጋግጧል። በዚህም መሠረት አቶ ጃዋር መንግሥት ሳይሆን በመንግሥት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሥጋት እንደሆኑበትና ለሕይወቱ ስለሚፈራ በግሉ ሐኪም ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን ቢስት እንኳን በመንግሥት ሐኪም መመርመር እንደማይፈልግ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። በጣም መታመሙን፣ ምግብ ሲመገብ እንደሚያስመልሰውና አሁን ላይ ደግሞ እያስቀመጠው መሆኑን አስረድቷል።

ዓቃቤ ሕግ በሰጠው አስተያየት ለአቶ ጃዋር ሕክምና እንዲያገኙ ተጠይቀው በግል ሐኪሜ ከልሆነ አልታከምም እንዳሉ ገልጿል። አቅርቦቱ እያለ አልፈልግም እያሉ ወደሌላ ሐኪም ቤት መውሰድ ሥልጣንን አላግባብ መጠቀም መሆኑን ጠቁሞ በሕግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል ነው የሚለውን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌም የሚጥስ መሆኑን አክሏል። ወደ ግል ሐኪም ሪፈር ሊደረጉ የሚችሉት ከመንግሥት ሕክምና በላይ የሆነ ሕክምና ሲያስፈልግ ብቻ መሆኑንም ተናግሯል።

ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 21 ድንጋጌ መሠረት አቶ ጃዋር በግል ሐኪም እንዲታዪ ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል። (ሪፖርተር – ታምሩ ጽጌ)

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top