Connect with us

የማሊው ‹‹መፈንቅለ መንግስት››

የማሊው ‹‹መፈንቅለ መንግስት››
BBC | The mutinying soldiers were cheered by crowds as they reached the capital Bamako

አለም አቀፍ

የማሊው ‹‹መፈንቅለ መንግስት››

የማሊው ፕሬዝዳንትን ከስልጣናቸው እንዲነሱ ያደረጉ ወታደሮች አገሪቱን ለምርጫ የሚያዘጋጅ የሲቪል የሽግግር መንግስት እንደሚቋቋም አስታወቁ፡፡

ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ኪዬታ ማክሰኞ ማምሻውን በመፈንቅለ መንግስት አድራጊ ወታደሮች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ የአገሪቱ ሕዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት እንዲበተን አድርገዋል፡፡

በአስር ሺህዎቸ የሚቆጠሩ ማሊያውያን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ኬይታ ከስልጣናቸው እንዲለቁ የሚጠይቁ ሰልፎችን በመላ አገሪቱ ለወራት ሲያደርጉ ከርመዋል፡፡

በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት የምጣኔ ሃብት እና የፖለቲካ ማሻሻያዎች እንዲደረግ በመንግሥት ላይ ጫና ቢያደርጉም፣ ፕሬዝዳንቱ በእምቢታቸው ጸንተው ቆይተዋል፡፡

በአገሪቱ የተባባሰው ኃይማኖታዊ አክራሪነት እና ጎሳን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች፣ ሙስና እና የተዳከመው የአገሪቱ ኢኮኖሚ ለሕዝባዊ ተቃውሞው መበርከት ምክንያት ሆኗል፡፡

እ.አ.አ ከ2013 ጀምሮ በስልጣን ላይ የነበሩትን ፕሬዝዳንት ኬይታን ከተቃዋሚዎች ጋር ለማደራደር ሲጥር የከረመው የምዕራብ አፍሪካ አገራት የምጣኔ ሃብት ማኅበረሰብ (ኢኮዋስ)፣ የወታደሮቹን እርምጃ የተቃወመ ሲሆን አባል አገራቱ ከማሊ ጋር የሚያዋስናቸውን ድንበሮች ዝግ እንዲያደርጉም ወስኗል፡፡

‹‹የወታደሮቹ እርምጃ ግልጽ የሆነ የመፈንቅለ መንግስት መከራ ነው›› ያሉት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ለቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት፣ በቁጥጥር ስር የሚገኙት ፕሬዝዳንት ኪዬታ እና የካቢኒያቸው አባላት እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት በአገሪቱ በተፈጠረው ሁኔታ ላይ ዛሬ እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡ (አሐዱ ራድዮ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top