Connect with us

ዶክተሩ በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸው አለፈ

ዶክተሩ በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸው አለፈ
Photo: Social Media

ጤና

ዶክተሩ በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸው አለፈ

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት በኢፒዲምዮሎጂ ትምህርት ክፍል ባልደረባ የነበሩት ዶክተር ፍሰሃየ አለምሰገድ ተስፋሚካኤል (ተባባሪ ፕሮፌሰር) የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ሕብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ታመው የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በሃላ በቀን 01/12/2012 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በድንገት በሞት ተለይተዋል፡፡

ዶ/ር ፍሰሃየ በ1970 ዓ.ም በትግራይ ክልል ዓድዋ ወረዳ ልዩ ስሙ ይሓ በተባለ ቦታ ተወልደው ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የህክምና ትምህርታቸው በስኬት በመጨረስ በጠቅላላ ሓኪምና በሕብረተሰብ ጤና የኢፒዶሞሎጂ የማስተርስ ትምህርታቸውን አጠናቅቀዋል።

ዶ/ር ፍሰሃየ አለምሰገድ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመምህርነት፣ በተማራማሪነትና በሙያ እማካሪነት ከ1994 ዓ/ም እስከ 2011 ዓ/ም ካገለገሉ በኃላ ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በመዛወር በዩኒቨርሲቲው የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ዶ/ር ፍሰሃየ በእናቶችና ህፃናት ህክምና፣ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች፣ በስነ-ምግብ፣ በወባ፣ በኤች አይቪ ኤድስና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ጨምሮ በሌሎች የሕብረተሰብ ጤና ዘርፎች ከ50 በላይ ችግር ፈቺ ጥናቶችን በታዋቂ ጆርናሎች በማሳተም አዳዲስ እውቀቶች በማፍለቅ ለዓለም አሻራቸውን አሳርፈዋል።

ዶክተር ፍሰሃየ አለምሰገድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ፈጣን ግብረ መልስ ቡድን መሪ በመሆን ህዝባቸውን ከቫይረሱ ለመታደግ ሌተቀን ሲሰሩ ቆይተው የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ባደረገላቸው ጥሪ በኮሮና ቫይረስ መረጃ ትንተና እና ትንበያ ክፍል በመስራት ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ህክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።( #Hakim)

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top