Connect with us

የጆርጅ ጨቅላ ሴት ልጅ:-“አባቴ አለምን ቀይሯል…”

የጆርጅ ጨቅላ ሴት ልጅ:-"አባቴ አለምን ቀይሯል..."
Photo: Facebook

አለም አቀፍ

የጆርጅ ጨቅላ ሴት ልጅ:-“አባቴ አለምን ቀይሯል…”

የጆርጅ ጨቅላ ሴት ልጅ:-“አባቴ አለምን ቀይሯል…”
(ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ)

በአሜሪካው ሚኒሶታ ግዛት በነጭ ፖሊስ ወላጅ አባቷን የተነጠቀችው የሟቹ ጆርጅ ፍሎይድ ጨቅላ ልጅ ስለ አባቷ ማንነት ለመጀመሪያ ጊዜ ተናገረች።

እንደ አሜሪካው ብሮድክስቲንግ ኮርፖሬሽን ( ኤቢሲ) ዘገባ የስድስት አመቷ የሟች ጆርጅ ልጅ፣ጂያና(ጂጂ) ጆርጅ ወላጅ እባቷ እንዴት እንደሞተ እና በማን እንደሞተ አታውቅም ነገር ግን የምታውቀው ነገር ቢኖር ሁሉም ሰው የአባቷን ስም ደጋግሞ እየጠራ መሆኑን ተገንዝባለች።

ከወላጅ እናቷ ጋር “እንዴት አደርሽ አሜሪካ”(ጉድ ሞርኒግ አሜሪካ)በተባለው ፕሮግራም የቀረበችው ጨቅላዋ (ጂጂ)ስለ አባቷ “አባቴን በእጅጉ እናፍቃለሁ፣ አባቴ ሁሌም ሳይሰላች የሚያጫውተኝ፣ ቀልድ አዋቂ አባት ነበር” በማለት የአርባ ስድስት አመቱ አባቷን ዘክራዋለች። ከካሚራው ቀረጻ በሁዋላ ሰለ አባቷ ስትናገር ” አባቴ አለምን የቀየረ ሰው ነው “በማለት ደግማ ተናግራለች።

ወላጅ እናቷ ሮክሲ ዋሽንግተን እንዲሁ ” ጂጂ ለአባቷ፣ ለጆርጅ ልዩ ፍቅር አላት ሌላ ሰው እንኳን ሊያጫውታት ቢፈልግ ከአባቷ ውጪ እሺ አትልም፣ ምክንያቱም አባቷም ቢሆን በጣም ስለሚወዳት፣ ከትከሻው ላይ በማስቀመጥ አብዝቶ ሰለሚያጫውታት ነበር። እኔም ብሆን ጆርጅ መልካም ሰው በመሆኑ፣ በጣም ነው የምወደው፣ በዚያች የፖሊስ ባልደረባው ኤሪክን ‘መተንፈስ አልቻልኩም’ እያለ በሚማጸንበት የጭንቀት አዘል ደቂቃ ጆርጅን ከጎኑ ቆሜ ብረዳው በጣም ደስ ባለኝ ነበር። ጂጂ ሰዎች ሰለአባቷ ጆርጅ አጥብቀው ለምን እንደሚያወሩ ስትጠይቀኝ ጆርጅ መተንፈስ ተስኖት እንደሞተ አርድቻታለሁ “ብላለች።

ባለፈው ሰኞ ግንቦት/ሜይ 25,2020 እኤእ በአሜሪካው የሚኒሶታ ግዛት በነጩ የቀድሞ የፖሊስ አባል ፣ዴሪክ ቻአቨን እጅ ህይወቱ ያለፈው ጥቁር አሜሪካው ጆርጅ ፍሎይድ የሴት ልጁ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ወጥታ ይብዙዎችን ልብ የነካ ንግግር ያደረገችው የሴት ልጁ እናት ሮክሲ “እዚህ የቆምኩት ስለ ጨቅላዋ ልጄ እና ስለ ጆርጅ ፍትህ በመሻት ነው፣ ምክንያቱም ጆርጅ እጅግ በጣም ጥሩ ሰው ነው፣ ልጁ አድጋ ትምህርቷን ስትጨርስ፣ ስትመረቅ ጆርጅ ከጎኗ የለም፣ እዚህ ላይ ሁለም ሰው እንዲያውቅልኝ የምፈፈልገው ነገር ቢኖር እነዚያ የ ጆርጅ ህይወትን የቀጥፉት የፖሊስ አባላት ከቤተሰባቸው ጋር ሲቀላቀሉ፣ የጆርጅ ቤት ግን ዛሬ ባዶ መሆኑን ነው” በማለት የብዙዎችን ልብ የሰበረ እስተያየቷን ተናግራለች።

ለጆርጅ ሞት ምክንያት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩት አራቱም የፖሊስ አባላት ክስ እንዲመሰረትባቸው የሚኒሶታ አቃቢ ህግ ኬይዝ ኤሊሰን እሮብ ለዜና ሰዎች ተናግረዋል። በአዲሱ የክስ ቻርጅ መሰረት ጉልበቱን በጆርጅ አንገት ላይ የጫነው የቀድሞው ፖሊስ ዴሪክ ቀደም ሲል የተከሰሰበት የሶስተኛ ደረጃ ሰው የመግደል ወንጀል ተጠርጣሪነት ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ እንዲል የተደረገበት ሲሆን የተቀሩትም ሶስት የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር እንዲውል ማዘዣ የተተላለፈባቸው ሲሆን ተመሳሳይ የክስ ቻርጅ ይጠብቃቸዋል ተብሎ ይገመታል። ለአራቱም ተጠርጣሪዎች የአንድ ሚሊዮን ዶላር ዋስትና ተጠይቆባቸዋል።

የጆርጅ ቤተሰቦች ጠበቃ የሆኑት ቤንጃሚን ክራምፕ የፖሊሶቹን በቁጥጥር ስር መዋልን ” የጆርጅ ስርአተ ቀብር ከመከናወኑ በፊት የተከናወነ፣ ለፍትህ ፍለጋ የሚደረግ ጉዞ መንገድ ጠራጊ ነው” በማለት በመልካም ጎኑ የተመለከቱት መሆናቸውን ደስታቸውን ለዜና ሰዎች ተናግረዋል ስለጆርጅ ፍትህ የጠየቁትን ሁሉንም በማመስገን አመጻ እና አላስፈላጊ ፍጥጫዎች እንዳይፈጠሩ በጆርጅ ቤተሰቦች ስም ተማጽነዋል።

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top