Connect with us

አቶ በቀለ ገርባ አሉት ከተባለው ነገር ይልቅ …

አቶ በቀለ ገርባ አሉት ከተባለው ነገር ይልቅ

ፓለቲካ

አቶ በቀለ ገርባ አሉት ከተባለው ነገር ይልቅ …

አቶ በቀለ ገርባ አሉት ከተባለው ነገር ይልቅ ያሉትን ነገ ስላለመቀየራቸው ዋስትና ስለሌለን አንቀየማቸው፡፡
ወያኔ ገራፊ ነው ያሉን እሳቸው ውሸት ነውም ያሉት እሳቸው ደግሞ ነገ የሚሉትን አብረን እንሰማለን
******
ከስናፍቅሽ አዲስ

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጥቂት ሰዎች ትናንትናቸውን ነገ አይደግሙትም፡፡ ወያኔ ገራፊ ጨካኝ አኮላሽ የሚባለው ስም በብዛት የገነነው የአቶ በቀለ ገርባን እስር ተከትሎ እንደ ቪኦኤ ያሉ መገናኛ ብዙሃን በሚሰጡት መረጃ ነበር፤ የመረጃው ምንጭ ደግሞ ሰውዬው ናቸው፡፡

ከእስር ከወጡ በኋላ ጀግናው ተብለው ሲሞገሱ ሊመርቃቸውና ሊያመሰግናቸው የመጣውን ወጣት በወያኔ ጥላቻ ክፋት ያስታጠቁት እሳቸው ናቸው፡፡ እዚህ ሀገር ወያኔ የገረፈው ህዝብ የለም፤ ተገረፍን ላሉ ፖለቲከኞች በመወገን የታመመ ህዝብ እንጂ፤
አቶ በለቀ ገርባ አሁን ያ ሁሉ ነገር ውሸት ነው ብለዋል፡፡ እንዲህ ማለታቸው ነውር የለውም፡፡ ወያኔ ያን አላደረገም ብሎ ማመንም መመስከርም ይችላሉ፡፡ ጥፋታቸው አንድ ነው ከዚህ ቀደም አድርጓል ብለው የነበሩትን አምነን ነበር የአሁኑን ድጋሚ ላለመቀየራቸው ምን ዋስትና አለ?

በሌላ በኩል አቶ በቀለ ወያኔ ገራፊ አይደለም ብለውናል፤ ለወያኔ ያልተለጠፈ ስም አለመኖሩንም ነግረውናል፡፡ እርግጥ ከእኛ ቀድመው የፓርቲያቸውን አባል አቶ ጃዋር መሐመድን ቢያሳምኑት መልካም ነው፡፡ መቼም እዚህ ሀገር በጌታቸው አሰፋ ጣቱን ያልቀሰረ የለም፡፡ እንደ እሳቸው ሁሉ አቶ ጃዋርም በዋልታ ቲቪ ቀርቦ ሲናገር እዚህ ሀገር እነ ጌታቸው አሰፋ ያልሰሩት ስራ የለም ብሎ ማኮላሸታቸውን መግረፋቸውንና ማሰቃየታቸውን ተናግሯል፡፡ አጠገቡ ያለውን ጓድ ያላሳመነው አቶ በቀለ አደባባይ ወጥቶ ውሸት ነው ብሎ የሚናገረው ለማን ነው?

አቶ በቀለ ወያኔ ገራፊ አይደለም ብሎ ለእኛ ሌላ ነገር ከመንገሩ በፊት አስቀድሞ ስም ያጠፋው እሱ ነውና ወያኔን ገራፊ አሰቃይ ጨካኝ አድርጌ መክሬ መንገድ ላዘጋኋቸው ወጣቶች ጥፋተኛው እኔ ነኝና ይቅር በሉኝ ብሎ ወያኔን ይቅርታ መጠየቅ አለበት፡፡ ከዚያ ማረሚያውን እኛ እንቀበላለን፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top