Connect with us

አዋጁን በማያከብሩት ላይ አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንወስዳለን

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማያከብሩት ላይ አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንወስዳለን

ፓለቲካ

አዋጁን በማያከብሩት ላይ አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንወስዳለን

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማያከብሩት ላይ አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንወስዳለን … የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተከለከሉ ድርጊቶች የማይቆጠቡት ላይ አስተማሪ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ፡፡

አቶ ሽመልስ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ ሀይል ስራው ያለበትን ደረጃ በገመገመበት ወቅት ባደረጉት ንግግር “የኮሮና ቫይረስ /ኮቪድ-19/ ስርጭቱ እየሰፋ መምጣቱ ልዩ ትኩረት የሚሻው ጉዳይ ነው” ብለዋል፡፡

ኮቪድ 19- በዓለም ላይ እያሳደረ ያለውን ጉዳት እያዩ ያለንበትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመተላለፍ የቫይረሱ ስርጭት እንዲባባስ በሚያደርጉ ሰዎች ላይ አስተማሪ የሆነ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በሌላ በኩል የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎችን ከቤት በመደበቅ በሽታው እንዲስፋፋ እያደረጉ ያሉ ሰዎች ላይም አስፈላጊው እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመከላከል ከገበያ ስፍራዎች ጋር በተያያዘ ያለው እንቅስቃሴ የተሻለ ቢሆንም ከበሽታው ክብደትና የስርጭት ባህሪይ ጋር ሲነፃፀር በቂ እንዳልሆነም ገልፀዋል፡፡

የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የኑሮ ውድነት እንዲፈጠር በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይም የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢንዱስትሪዎች ሥራ ማቆም እንደሌለባቸው የገለፁት ፕሬዚዳንት ሽመልስ፤ ሰራተኞች ከበሽታው ራሳቸውን የሚጠብቁበት ሁኔታን የማመቻቸት ስራ ቀጣይነት እንዲኖረው አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ወቅቱ ግንቦት ወር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በድርቅ ምክንያት የውሀ እጥረት እንዳያጋጥም ሁሉም አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸውም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

“እንደ ክልላችን የኢኮኖሚ ውድቀት እንዳያጋጥም በየትኛውም መስክ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው መቆም የለበትም” ብለዋል።
የኮቪድ 19 አደገኛነትና የስርጭቱን ፍጥነት በመገንዘብ የእምነት አባቶች፣ ህዝብና በረመዳን የጾምና ሶላት ወር ውስጥ የሚገኙ የእምነት ተቋማት አጥብቀው እንዲፀልዩ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ አቶ አዲሱ አረጋ በዚህ ወቅት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ቤት ለቤት በተሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ 33.5 ሚሊዮን ሰዎች ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ስድስት መቶ የገበያ ስፍራዎች የተዘጋጁ መሆኑንም ገልፀው፣22 ሆስፒታሎችም ኮሮና ቫይረስ ላይ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ ሙሆኑንም ገልፀዋል፡፡(የክልሉ ኮሙዩኒከሽን ቢሮ)

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top