Connect with us

“ብስጭት ያስፈልገናል!”

Ethiopian press agency

ነፃ ሃሳብ

“ብስጭት ያስፈልገናል!”

“ብስጭት ያስፈልገናል!”
(ጋሻው መርሻ)

ወያኔ ግዙፍ እና አቅም ያለው ቡድን አይደለም። አንዳንድ ሰዎች ወያኔን በጣም ጠንካራ እና የማይደፈር አድርገው ለማቅረብ ይሞክራሉ። ይህ በፍፁም ስህተት ነው። ወያኔ ይህን መሰል ወረራ ሊፈፅምብን የመቻሉ ምስጢር ወያኔ ጠንካራ ስለሆነ ሳይሆን እኛ ስላልተዘጋጀን ብቻ ነው።

ልዩነቱ የመዘጋጀት እና ያለመዘጋጀት ጉዳይ ነው። ወራሪው ቡድን ወረራ ለመፈፀም ቀደም ብሎ ሁሉንም የትግራይ ህዝብ አንቀሳቅሶታል። ሴት ወንድ፣ ህጻን ሽማግሌ፣ ምሁር ያልተማረ፣ ዲያስፖራ ሀገር ቤት ያለ ሳይል ሁሉንም አቅሙን ዩትላይዝ አድርጓል።

ደባርቅ አካባቢ አንድ ትልቅ ሰው ወያኔዎች ከሁለት ዓመታት በፊት ጀምረው አህያ በመኪና እየጫኑ ወደ ትግራይ ሲያግዙ ተመልክተው እነዚህ ሰዎች ወረራ ሊፈፅሙብን ስለሚችሉ እባካችሁ ተዘጋጁ ማለታቸውን ሰምቻለሁ።

እኝህ ትልቅ ሰው ሰዎቹ አህያን ለገጠር ጭነት እንደሚጠቀሙ እና በብዛት አህያ ከጫኑ ለጦርነቱ ግባት እንደሚሆን የቆዬ ልምዳቸው አስተምሯቸዋል። ያሉት አልቀረም አህያን ዋና የጭነት መገልገያ አድርገው መጥተዋል።

በእኛ በኩል ብዙ መዝረክረኮች ነበሩ። አሁን እነዚህ ሁሉ መዝርክረኮች በሚገባ እየተቀረፉ ነው። ለእስካሁኑ ሽንፈታችን በራሳችን ውስጥ ሰርገው የገቡ ባንዳዎች እና ወያኔዎች ትልቅ እጅ ነበራቸው።

ባንዳዎቹ ከመጀመሪያው ቀን ጀምረው ይኸ ጦርነት የህልውና ጦርነት ሳይሆን የስልጣን ሽሚያ እና ፉክክር ነው እያሉ ህዝባችን በግማሽ ልቡ እንዲታገል መስተሃሊውን ሲከፍሉት ነው የከረሙት። ቀርፋፋው መንግስታችንም በጎን ክተት፣ ዝመት፣ ወጥር እያለ በሌላ ጎን ይኸ ጦርነት አይመለከትህም እያሉ የተዋጊውን ልብ የሚያሸፍቱትን ታቅፎ ያድራል።

ጦርነቱ የህልውና ሳይሆን የአዘቦት ጦርነት እስኪመስል ድረስ ሁሉም በየአፉ የሚያመነዥከው ሆኖ ከረመ። ብዙ ወገኖች ተዋጊው ኃይል በሚገባ እንዲዋጋ፣ ህዝባችን በሚገባ ደጀን ይሆን ዘንድ በአንድ እዝ ጠገግ ስር ገብቶ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ይጠርነፍ እያሉ ብዙ ጩኸው ነበር።

ዘግይቶም ቢሆን አሁን ላይ ይህ እየተገበረ ይገኛል። ጦርነቱ አይመለከትህም ባዮችንም አደብ ማስገዛት የግድ ነው። እያለቀ ያለው ህዝባችን ስለማይመለከው አለመሆኑን ማሳየት ይገባል።

በዚህ የህልውና ዘመቻ ላይ የምንቆጥበው አንዳችም ነገር መኖር የለበትም። ገንዘባችን፣ እውቀታችን፣ ጉልበታችን፣ ህይዎታችን ሁሉ ለነጻነታችን ማበርከት ይኖርብናል። ነጻነት በነጻ አይገኝም እያሉ መተረት ብቻ ነጻ አያደርግም።

ደሴ እና ኮምቦልቻ ላይ ጦሩ ሲበተን የነበረውን የህዝብ ዋይታ ለተመለከተ ፍጡር ተኝቶ ማደር ስቃይ እንጅ እረፍት ሊሆነው አይችልም። የሰሜን ወሎ እናቶችን መከራ፣ የጠለምት እና አድርቃይ ወገኖቻችንን በብረት መዳፍ ስር መኖር በእዝነ ህሊናችን እያሰብን በቃን ማለት አለብን።

የእህቶቻን ሰቆቃ፣ የአባቶቻችን ቅስም መሰበር፣ የእናቶች በቅኝ ግዛት ስር ኑሮን የማሸነፍ ግብግብ፣ የወንድሞቻችን አንገት መድፋት የሆነ ጊዜ እና ቦታ ላይ ሊቆም ይገባል ማለት አለብን። ይህ እንዲሆን ደግሞ በቃ የሚል ብስጭት ያስፈልገናል። ካልተበሳጨን ልናሸንፍ አንችልም።

እናሸንፋለን…!

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top