Connect with us

የህገ-መንግስት ጉዳይ  ከወያኔ አንፃር!

የህገ-መንግስት ጉዳይ  ከወያኔ አንፃር!

ህግና ስርዓት

የህገ-መንግስት ጉዳይ  ከወያኔ አንፃር!

የህገ-መንግስት ጉዳይ  ከወያኔ አንፃር !
(ታዬ ደንደአ ~ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር)

የኢፌዴሪን ህገ-መንግስት እንደወያኔ የጣሰ የለም። እንደወያኔ በህገ-መንግስቱ ስም የማለም የለም! በጌትነት ዘመኑ “ህገ-መንግስት ማስከበር” በሚል የንፁኃን ዜጎችን ህገ-መንግስታዊ መብቶች ጨፍልቆ ከፊሉን አስሮ ሲገርፍ፣ ከፍሉን አሰቃይቶ ሲያኮላሽ፣ ከፊሉን በጥይት ሲገድል እንደነበር ዓለም ያዉቋል። በህገ-መንግስት ስም ህገ-መንግስቱን እንዳልነበረ አድርጓል።

አሁንም በህገ-መንግስት ስም ህገ-መንግስቱን መቃወም ቀጥሏል። የትላንቱን የፓርላማ ክርክር ማየት ብቻ የወያኔ ምንነት እና ማንነት በጥልቀት ያስተምራል። ውሸት እና ማስመሰል አንዴ ባህል ከሆነ አይለቅም ይባላል!

ማንኛዉም ህግ( ህገ-መንግስትን ጨምሮ) በተለያዩ ምክንያቶች ለትርጉም ይቀርባል። የህግ ዝምታ፣ አሻሚ ትርጉም፣ የሚጋጩ ድንጋጌዎች እና ኢ-ምክንያታዊ ይዘት ህግ ከሚተረጎምባቸዉ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ። የአሁኑ የኢትዮጵያ ሁኔታ በህግ ዝምታ ይገለፃል።

ህገ-መንግስቱ በአንቀፅ 54 ምርጫ በየአምስት ዓመቱ መደረግ እንዳለበት እና በአንቀፅ 93 በመደበኛ አካሄድ ቁጥጥር ስር ሊዉል የማይችል ሁኔታ ሲያጋጥም አስቸኳይ ጊዜ ማወጅ እንደሚቻል ደንግጓል። ነገር ግን ምርጫና አስቸኳይ ጊዜ ሲደራረቡ መዉጫዉ ምን እንደሆነ አያሳይም። ይህ የህግ ዝምታ ክፍተት ይባላል። ችግሩን ለመፍታት የህገ-መንግስት ትርጉም መጠየቅ አግባብ ይሆናል። ወያኔ ግን ህገ-መንግስቱ ግልፅ ስለሆነ የግድ ምርጫ መደረግ አለበት ይላል።

እንደባህሉ ዛሬም በህገ-መንግስት ስም ዜጎች በኮሮና እንዲሞቱ ይፈርዳል። ህገ-መንግስቱ በግልፅ ተርጉሙኝ ብሎ የደነገገዉን እያዬ ተቃዉሞ በህገ-መንግስት ላይ ያልተመለከተዉን ክልል ላይ ምርጫ ለማካሄድ በስራ አስፈፃሚዉ ይወስናል!

ለማንኛዉም ወያኔ ራሱን ቢመረምር ይሻላል። ፍላጎቱን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚጭንበት ዘመን ዳግም ላይመለስ ሄዷል።

ያለአግባብ ይዞት ያለአግባብ ሲጠቀምበት ከነበረዉ ስልጣን የለቀቀዉ ወዶ ሳይሆን በነፃነት ፈላጊ ኢትዮጵያዊያን ትግል መሆኑን ቢያስታውስ ጥሩ ይሆናል። ያንን ቢገነዘብ ከአጉል መንጠራራት ይታቀባል። ከአሁን በኋላ ኢትዮጵያዊያን ለየትኛዉም አምባገነን ላይገዙ ወስኗል! ህገ-መንግስትም የዜጎችን ጥቅም እና ፍላጎት በሚያስከብርበት መንገድ ብቻ ይተገበራል!

ሠላም ዋሉ!

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top