Connect with us

ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 75 ደረሰ

ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 75 ደረሰ

ጤና

ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 75 ደረሰ

በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 75 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች መገኘታቸውንም አስታወቀ ።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸውአንድ ሺ 560 ሰዎች መካከል ሁለት ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁለቱም ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ፣ ምንም አይነት የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።

አንደኛው የ49 ዓመት የባቱ/ ዝዋይ ነዋሪ ሲሆን በአዲስ አበባ ህክምና በመከታተል ላይ የነበረ ነው። ሁለተኛዋ የስልጤ ወረዳ /የስልጤ ዞን ነዋሪ የሆኑ የ45 ዓመት ሴት ሲሆኑ በቤት ለቤት ቅኝትና አሰሳ የተለዩ መሆናቸውም ተገልጿል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ተጨማሪ ስድስት ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን አስታውቀው፤ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 75 መድረሱንም አመልክተዋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 135 መሆኑን ፣ ከእነዚህም ውስጥ 55 ሰዎች በለይቶ ህክምና ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በቫይረሱ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለት የውጭ አገር ሰዎች ደግሞ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ አይዘነጋም።

አዲስ ዘመን ሚያዝያ 26/2012

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top