Connect with us

ማይክ ፖምፒዮ ኮቪድ 19 ከውሀን ላብራቶሪ አምልጦ ስለመውጣቱ ግልፅ ማስረጃ አለን አሉ

ማይክ ፖምፒዮ ኮቪድ 19 ከውሀን ላብራቶሪ አምልጦ ስለመውጣቱ ግልፅ ማስረጃ አለን አሉ
Secretary of State Mike Pompeo pauses while speaking at a news conference at the State Department on April 29, 2020, in Washington, D.C. ANDREW HARNIK/Getty Images

አለም አቀፍ

ማይክ ፖምፒዮ ኮቪድ 19 ከውሀን ላብራቶሪ አምልጦ ስለመውጣቱ ግልፅ ማስረጃ አለን አሉ

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ኮሮና ቫረስ ከቻይናዋ ውሀን ግዛት ከገሚገኘው ላብራቶሪ ስለመውጣቱ ማስረጃ አለን በማለት ለስካይ ኒውስ ተናግረዋል፡፡

ከ 3 ቀናት በፊት ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራፕ ከማይክ ፖምፒዮ ጋር ተመሳሳይ አቋም ማራመዳቸው ይታወቃል፡፡

ትራምፕ ቫይረሱ ከቻይና ላብራቶሪ አምልጦ ስለመውጣቱ ማስረጃ አለን በማለት ተናግረዋል፡፡

ፖምፒዮም ይህንኑ ንግግር ከስካይ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስረድተዋል፡፡

ይሁን እንጂ የባለስልጣናቱ አስተያየት ከአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሪፖርት ጋር ይቃረናል፡፡

ተቋሙ በሪፖርቱ እንዳለው ኮሮና ቫይረስ ሰው ሰራሽ አልያም በዘረ-መል የተሻሻለ አይመስልም ብሏል፡፡

የስካይ ኒውሱ ጋዜጠኛ በጥቄው የአሜሪካ የስለላ ድርጅት መደምደሚያ ላይ አለመድረሱን በጠየቀ ሰዓት ፖምፒዮ ሲመልሱ የስለላ ማህበረሰቡ የተናገረውን ንግግር አይቻለሁ፡፡ እነርሱ ተሳስተዋል ብዬ ለማመን ምንም ምክንያት የለኝም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

እርሳቸው አለን ላሉት ማስረጃ ግን ዝርዝር ነገር ለመናገር ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡

(ኢትዮ ኤፍ ኤም )

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top