Connect with us

ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚውሉ የፊት ጭምብሎች ጥራታቸውን ጠብቀው መዘጋጅት እንዳለባቸው ተገለጸ

ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚውሉ የፊት ጭምብሎች ጥራታቸውን ጠብቀው መዘጋጅት እንዳለባቸው ተገለጸ
Wearing a cloth face mask does not replace any of the other recommended safety measures, but experts now believe it is better than leaving your home with a bare face.PHOTOGRAPH: MARCO BERTORELLO/GETTY IMAGES

ጤና

ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚውሉ የፊት ጭምብሎች ጥራታቸውን ጠብቀው መዘጋጅት እንዳለባቸው ተገለጸ

ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚውሉ የፊት ጭምብሎች ጥራታቸውን ጠብቀው መዘጋጅት እንዳለባቸው ተገለጸ

ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚያገለግሉ የፊት ጭምብሎች የጥራት መስፈርቶችን አሟልተው መዘጋጀት እንዳለባቸው ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የኮቪድ 19 ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ጥቅም ላይ ከሚውሉ ግብዓቶች አንዱ የፊት ጭምብል ሲሆን በርካታ የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎችና ግለሰቦች ይህን ጭምብል በማምረት ላይ እንደሚገኙ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ ገልጸዋል ፡፡

ከወረርሽኙ አስከፊነት የተነሳ ከምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ፈቃድ ሳያስፈልጋቸው ከጨርቅ የሚሰሩ የፊት ጭምብሎች የጥራት መስፈርቶችን አሟልተው መዘጋጀት ያለባቸው ሲሆን ለእነዚህ የፊት ጭምብሎች መስሪያነት የሚውል ጨርቅ 100% ጥጥ ወይም ከዚህ ጋር ተመጣጣኝ የመከላከል አቅም ያላቸው የልብስ አይነቶች መሆን ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ከጨርቅ የተሰሩ የፊት ጭምብሎች በላውንደሪ መታጠብ፣ መተኮስና መቀቀል የሚችሉ፣ ፊት ላይ ሲደረጉ ምቾት የማይነሱ፣ ለልጅና ለአዋቂ የፊት መጠን የሚስማሙ፣ መተንፈስ የማይከለክሉ፣ በቀላሉ የማይቀደዱ እንዲሁም ብናኝና በካይ ነገሮች የሌላቸው መሆን እንዳለባቸው የተናገሩት ዳይሬክተሩ በምንም አይነት በዓይን የሚታይ ቀዳዳ ወይም እንከን የሌላቸው፣ ተለጣጭ ማንጠልጠያ ያላቸውና ከእርጥበት ነፃ መሆን እንደሚገባቸውም ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የምርት ስምና አይነት፣ የአምራቹ ስምና አድራሻ፣ የህክምና ጭምብልን የማይተካ መሆኑን የሚገልጽ፣ አጠቃቀሙንና ለህክምና አገልግሎት ጥቅም የማይውል መሆኑን የሚገልጽ ጽሁፍ በምርቱና በማሸጊያው ላይ መያያዝ እንዳለበትም አቶ ወንድሙ ጠቅሰዋል፡፡

በመጨረሻም በገላጭ ጽሁፉ ላይም ሆነ በማስታወቂያ ከህክምና ጭምብሎች እኩል አገልግሎት እንዳለው፣ የኮቪድ 19 ቫይረስ መዛመትን ሙሉ በሙሉ እንደሚከላክል፣ ሌሎች የመከላከያ ጥንቃቄዎችን እንደሚተካ እና መሰል አሳሳች መረጃዎችን ለህብረተሰቡ አቅርቦ የተገኘ አምራች ላይ አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመው ከጨርቅ የተሰራ የፊት ጭምብል ብቻውን የቫይረሱን ስርጭት ስለማይከላከል ህብረተሰቡ አካላዊ ርቀትን ከመጠበቅና ቤት ከመቀመጥ ጎን ለጎን ሰው በበዛበት አካባቢና በግብይት ስፍራዎች የፊት ጭምብል በማድረግ ራሱንና ወገኑን ከቫይረሱ ይጠብቅ ሲሉ አቶ ወንድሙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

(ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር)

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top