Connect with us

ኮሮናን ለመግታት የመንግስት መመሪያዎችን መተግበር ወሳኝ ነው

ኮሮናን ለመግታት የመንግስት መመሪያዎችን መተግበር ወሳኝ ነው ... የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
Photo Facebook

ዜና

ኮሮናን ለመግታት የመንግስት መመሪያዎችን መተግበር ወሳኝ ነው

የኮሮና ቫይረስ ን ለመግታት በመንግስት የሚተላለፉ መመሪያዎችን መተግበር ወሳኝ መሆኑን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ።

የኢንስቲትዩቱ አባላት ቡድን እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮሮና ቫይረስ መከላከል ግብረኃይል የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለቫይረሱ መከላከል ያደረገውን ዝግጅት ትናንት ጎብኝተዋል፡፡

በዚህ ወቅት በኢንስቲትዩቱ የማህበረሰብ ጤና ተመራማሪ አቶ የሻምበል ወርቁ እንደተናሩት በሃገሪቱ በሽታው የከፋ ጉዳት ሳያስከትል ለመቆጣጠር መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ተቀናጅተው እየሰሩ ነው፡፡

መስሪያ ቤታቸውም እንደቫይረሱ ስርጭት መጠን የመመርመሪያ መሣሪያ በፍትሃዊነት ለማድረስ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡

ሆኖም የኢንስቲትዩቱ ኣባላት ቡድን ሰሞኑን በአሶሳ ከተማ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኙ አካባቢዎች ዳሰሳ ማድረጉን የገለጹት ተመራማሪው በዚህም ስለቫይረሱ ምንም ግንዛቤ የሌላቸው ማህበረሰቦች እንዳሉ ማስተዋላቸውን ጠቁመዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ለመግታት በመንግስት የሚተላለፉ መመሪያዎችን መተግበር ወሳኝ መሆኑን ገልጸው

“በተለይም በሃገሪቱ ቫይረሱ ያልተከሰተባቸው አካባቢዎች በሽታውን አስቀድመው ለመከላከል ያላቸውን እድል ሊጠቀሙ ይገባል “ብለዋል፡፡

ዕድሉን ለመጠቀም ደግሞ ከማህበረሰብ እስከ አመራር ስለቫይረሱ ግንዛቤ የመፍጠር ጥረታቸውን የበለጠ ማጠናከር እንዳለባቸውም አመልክተዋል፡፡

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ኃይማኖት ዲሳሳ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የለይቶ ማቆያ፣ የማከሚያ እና የማገገሚያ ማዕከላትን መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የተመረተውን ሳኒታይዘር ጨምሮ የተለያዩ የንጽህና መጠበቂ እና የህክምና ቁሳቁሶች መሟላታቸውንም አስረድተዋል፡፡

በአከባቢው አሁንም አካላዊ ርቀትን ያለመጠበቅን ጨምሮ የህብረተሰቡ መዘናጋት በቫይረሱ መከላከል ሂደት ዋነኛ ስጋት መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቫይረሱ መከላከል ግብረ ኃይል የሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን አባል አቶ መለሰ በየነ ናቸው፡፡

ግብረ ኃይሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራን የበለጠ ማጠናከር እንደመፍትሔ አድርጎ እየሠራ መሆኑን ጠቁመው ህብረተሰቡ ከምንም በላይ በሽታውን ለመከላክ የተላለፉ መመሪያዎችን ማክበርና መተግባር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በክል ቫይረሱን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ እያገዘ መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢዜአ ሚያዚያ 12 / 2012

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top