Connect with us

ፕሬዝዳንት ትራንፕ ወደ አሜሪካ የሚደረግ ጉዞ ሊያግዱ መሆኑን አስታወቁ

ፕሬዝዳንት ትራንፕ በኮሮና ምክንያት ወደ አሜሪካ የሚደረግ ጉዞ ሊያግዱ መሆኑን አስታወቁ
Photo The White House

ዜና

ፕሬዝዳንት ትራንፕ ወደ አሜሪካ የሚደረግ ጉዞ ሊያግዱ መሆኑን አስታወቁ

ፕሬዝዳንት ትራንፕ በኮሮና ምክንያት ማንኛውንም ወደ አሜሪካ የሚደረግ ጉዞ ሊያግዱ መሆኑን አስታወቁ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶላንድ ትራምፕ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ወደ አሜሪካ የሚደረጉ ጉዞዎችን ሊያግዱ መሆኑን አስታውቀዋል።

ፕሬዝደንቱ በቫይረሱ ስርጭት ምክንያት ወደ አሜሪካ የሚደረጉ ጉዞዎችን ላልተወሰነ ጊዜ ለማገድ የሚያስችላቸውን ፕሬዝዳንታዊ ትእዛዝ እንደሚፈርሙ አስታውቀዋል።

ፕሬዝደንቱ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ አይስጡ እንጂ በክልከላው ላይ የተማሪ ቪዛ ያላቸው እና ለሥራ ወደ አሜሪካ የሚያቀኑ እገዳው አይመለከታቸውም ተብሏል።

ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ውሳኔያቸው የአሜሪካውያንን የሥራ እድልንም እንደሚያስጠብቅ ጠቅሰዋል።

የትራምፕ ተቺዎች ግን ፕሬዝደንቱ ኮሮናቫይረስን ምክንያት በማድረግ የሌላ አገር ጥገኘነት ጠያቂዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያዙት እርምጃ ነው እያሉ ነው።

የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ትራምፕ ከዚህ ቀደም ከአውሮፓ፣ ቻይና፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ለሚደረጉ ጉዞዎች ድንበራቸውን ዝግ አድርገዋል።

ከአንድ ወር በፊትም የአሜሪካ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች የቪዛ ቀጠሮዎቻቸውን ዝግ ማድረጋቸው ይታወሳል።

አሜሪካ እስካሁን 792,938 በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ያላት ሲሆን 42,518 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምንክያት ህይወታቸውን አጥተዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top