Connect with us

እንጦጦን አየሁት፤ የነገዋ አዲስ አበባ ታድላለች፡

እንጦጦን አየሁት፤ የነገዋ አዲስ አበባ ታድላለች
Photo: Social media

መዝናኛ

እንጦጦን አየሁት፤ የነገዋ አዲስ አበባ ታድላለች፡

እንጦጦን አየሁት፤ የነገዋ አዲስ አበባ ታድላለች
ተፈጥሮ፣ ቅርስና ጤና…  ነገ መልካም ይኾናል

ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩትን የእንጦጦ መናፈሻን አየሁት ሲል አዲሱን የተራራ ፕሮጀክት የደረሰበትንና የነገ ተስፋውን በተከታዮ ዘገባው እንዲህ ይነግረናል፡፡
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

እንጠጦ ያው የትናንቱ ተራራ ነው፡፡ የዛሬው ነገሩ ልዩ ነው፤ የነገውን ደግሞ ገምቻለሁ፡፡ ብዙ ሰዎች እዚህ ተራራ ላይ ተአምር እየተሰራ መኾኑን በማህበራዊ ሚዲያ ሰነግሩን ሰንብተዋል፡፡ ማየት አለብኝ ብዬ ወደ አዲስ አበባ አናት ወጣሁ፡፡ እንደ ስፍራው ከፍ ያለ ነገር ነበር የተመለከትኩት፡፡

እንጦጦ ድንቅ ነገር እየተሰራበት ነው፡፡ ነገ እየተሰራበት ነው፡፡ እኔ ሀገር ዛሬ እየተሰራ ሁሌም ዓለም ሲቀድመን ኖሯል፡፡ ዓለም ኖሮት የሌለን ብዙ ነው፡፡ ኖሮን ያጣን መኾናችን ደግሞ ቁጭቱን እጥፍ ያደርገዋል፡፡ አንድ ከቁጭት የሚያድን የትውልድ ኩራት በታላቁ የመዲናዋ ትከሻ ላይ አየሁ፡፡

ውስጡ ድንቅ አስፋልት ተሰርቶበታል፡፡ አስፋልቱ የእግረኛና የሳይክል ነው፡፡ ብዙ ፕሮጀክቶችን ያካተተው የእንጦጦ ፓርክ ልማት ከተሜን ከተፈጥሮ የሚያስተዋውቅ እንደኾነ አየሁ፡፡ ፈረስ መጋለቢያዎች፣ የስፖርት ማእከላት፣ የእግር ጉዞ ማረፊያዎች፣ የውሃ መስህቦች ብቻ ብዙ ነው፡፡ የሀገራችን ቅንጡ ሎጂ እዚህ ድንቅ የጎብኚ ማረፊያ እየሰራ ነው፡፡ አዲስ አበባ እንደ ፓሪስ ከፍ ያለ ማማ ባይኖራት እንኳን “አዲስ አበባን አውቃታለሁ” የሚል “እንጦጦ የተፈጥሮ ማማ ላይ ያለው ካፌ ኾነህ አይተሃታል?” ተብሎ ይጠየቃል፡፡ ህይወትና ደስታ እዚህ ደን ውስጥ ልትመሽግ ጥቂት ቀርቷታል፡፡

እንዲህ ያለው ጸጋ ለሌላው ዓለም ቅንጦት አይደለም መሰረታዊ ፍላጎት ነው፡፡ እንጦጦን መጠበቅ ብቻውን ድል ነበር፡፡ ይሄ እጥፍ ድል የሚያደርገው እንጦጦን መጠበቅ አልምቶ መጠቀም አዲስ አበባ የመጣ የውጪ ጎብኚን ሳይቀር አንድ ቀን የሚያሳድር ልዩ መስህብ ነው፡፡

እዚህ ታሪክ አለ፤ የአዲስ አበባ ቀደምቷ መዲና እዚህ ናትና፤ እዚህ ቅርስ አለ የታላቁ ጥቁር ንጉሥ የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ የዓይን ስስት የነበረችው እንጦጦ ማርያምና ሙዚየሟ የጉብኝት መስመሩ አካል ናቸውና፤ እዚህ ተፈጥሮ አለ፡፡ ሰው በዱር ውስጥ ከተፈጥሮ የሚነጋገርበት መስህብ ነውና፤

የእግረኛ ተጓዦች ማረፊያዎች ከቦሌ መንገድ ቅንጡ ካፊዎች ይበልጥ ያምራሉ፡፡ የሚታየው ሁሉ ደስ ይላል፡፡ ቀጣዩ ትውልድ ራሱን ከዓለም ከተሞች ጋር አንጽሮ የኔ ከተማ ውበትና ተፈጥሮስ ካለ እንጦጦ ጥሩ መልስ ይኾናል፡፡

 

ጠቅላዩ ናቸው የፕሮጀክቱ መሪ፣ ቤተ ሰሪ ደም የለውም የሚለው እዚህ ፕሮጀክት ላይ የታየው እፎይታም እንደሌለው ነው፡፡ የቀን ሰራተኞቹ እንደ ምጽአት ቀን ከተፍ ብለው የደረሰበትን ያያሉ አሉኝ፡፡ መምጫቸው አይታወቅም፡፡ ጠንካራ ሰዎች የሚመሩት ፕሮጀክት መኾኑ ጥራቱና ፍጥነቱ ይናገራል፡፡ ገና ግሩም ሀገር ደረቷን የምትነፋባቸው አፍሪቃዊ ፕሮጀክቶች እውን የሚኾኑበት ስፍራ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የጥበብ ቤተሰብ እንኳን በዚህ ዘመን መጣሁ የሚልበት ተአምረኛ ስራም ዱር ውስጥ ያለ ቡዘና እየተሰራ ነው፡፡ እዚህ ህይወት እጅግ ፈጣን ናት፡፡

እንጦጦ ሆይ ሆይታ የለውም፣ እንደ ዱሩ ሰላም በዝምታ የሚሰራ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑን ግን ተረድቻለሁ፡፡ ሲያልቅ ተራራ ረበሸን የሚሉ የሀገሬ ከንቲባዎች በየከተማቸው ያለውንና የጠሉትን ተራራ እንደ አልተነካ ሀብት ይቆጥሩታል፡፡ ያኔ እንጦጦ ተራራና መናፈሻ ብቻ ሳይሆን ትምህርት ቤትም ይኾናል፡፡

በመጨረሻም፤ እንደልብ ማየት በሚቻለው ስፍራ ፎቶ ማንሳት ስለማይፈቀድ የያሁትን ተአምር ምስሎች የወሰድኩት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌስ ቡክ ገጽ መኾኑን ለማሳወቅ እወዳለሁ፡፡

Click to comment

More in መዝናኛ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top