Connect with us

“ቴዲ የመርህ ሰው ነው!”

Social media

መዝናኛ

“ቴዲ የመርህ ሰው ነው!”

“ቴዲ የመርህ ሰው ነው!”
(ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ)

በትላንትናው ዕለት አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ቢሮ ያወጣው መግለጫ እጅግ በጣም አስደሳች ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ይኸውም ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ራስህን አክብረህ ሀገርሀን አስከብረሀልና የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ልንሰጥህ ስንወስን በኩራት ነው የሚል ይዘት ያለው መልክት ማስተላለፉ ነው።
ቴዲ አፍሮ የነጻነት ታጋይ በመሆኑ ክብር ለሚገባቸው ተገቢውን ክብር ሲሰጥ አይሰስትም፣ በዚህም መሰረት የአጼ ኃይለ ስላሴን፣ የአጼ ምኒልክን፣ የአጼ ቴዎድሮስን፣ የአትሌት ኃይሌ ገብረስላሴንና የአትሌት ቀነኔሳ በቀለን ስምና ገድል በማንሳት አወድሷቸዋል። ይህም ሁኔታው ብዙዎቻችን የሀገር ባለውለታዎችን ለማስታወስ በምንቸገርበት ወቅት እሱ ግን በድፍረትና በልበ ሙሉነት አስታውሶ እንዲታወሱ አድርጓል።
ይህ ድፍረቱና በራስ የመተማመን መንፈሱ ብዙዎቻችንን ቢያስደስትም ጥቂት እኩያንን ግን በእጅጉ አስከፍቷል። በዚህም ምክንያት በተደጋጋሚ ዋጋ እንዲከፍል አድርገዋል፣ ስለሆነም በሀገር ውስጥ ኮንሰርት እንዳያዘጋጅ ከመከልከል ጀምሮ አልበም እንዳያስመርቅ በማገድ ገንዘቡንና ሞራሉን በአያሌው ለመከሽከሽ ጥረት አድርገዋል። አልተሳካላቸውም እንጂ አፍቃሬ አጼዎች በማለትም ለማጥላላት ሞክረዋል።
ይኸ ሁሉ ሲሆን ቴዲ አንድም ቀን ከከፍታው ዝቅ ብሎ አያውቅም፣ በዚህ ክፉ ድርጊታቸው ተማሮም ውጭ አገር በሄደበት አጋጣሚ በዛው መቅረትን አላሰበም።
ሌላው ቀርቶ ሚኒስትሮችና ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት ሚስቶቻቸው ሲያረግዙ አሜሪካና እንግሊዝ አሊያም ካናዳ ሄደው እንዲወልዱ ሲያደርጉ ቴዲ ግን ሚስቱ ከአሜሪካ መጥታ አገሯ ላይ እንድትወል ወስኗል።

አገር መደድ ይኸ ነው።
በአጠቃላይ ቴዲ የመርህ ሰው ነው፣ ቴዲ የጥበብ ዛር የሰፈረበት በመሆኑ ጥበብን አክብሮ አስከብሯል፣ ቴዲ የፍቅር ሰው ነው፣ ይኸ ሁሉ በደል እየደረሰበት ፍቅር ያሸንፋል በማለት አዚሟል።
ቴዲ ሁለገብ ችሎታ ያለው ጥበበኛ ነው፣ በአንድ ቀን ሌሊት ለዘመናት ሲታወስ የሚኖር ነጠላ ዜማ ሰርቷል፣ ቀነኔሳ አምበሳ የሚለው ነጠላ ዜማ በዚህ መልክ የተገኘ ምርጥ ስራው እንደሆነ ይታመናልና ሊከበር ይገባል።

Click to comment

More in መዝናኛ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top