Connect with us

የልብ ገቢያው ወዴት ነው?

የልብ ገቢያው ወዴት ነው?

ጥበብና ባህል

የልብ ገቢያው ወዴት ነው?

የልብ ገቢያው ወዴት ነው? | ከሙሉጌታ ዜና የስነባህሪ ባለሞያ በድሬቲዩብ 

ብዙ ጊዜ በተለምዶው “እከሌ ልብ ገዛ” “እከሊት ልብ ገዛች” ተብሎ ይነገራል፡፡ የተለያየ ባህሪ ችግር ያለበትን ሰው ደግሞ አረ “ተው ልብ ግዛ” ይባለል፡፡ በአባባላችንም ገንዘብ በሃያ አመት ልብ በአርባ አመት ተብሎ ይነገራል፡፡ ይህንና የመሳሰሉ ስለ ልብ መግዛት የሚነገሩ አባባሎች በዘፈቀደ የተነገሩ አይመስለኝም፡፡

በእኔ አመለካከት በህይወት ገጠመኝ ካስተዋልናቸው እና ካሰለፍነው ስህተቶች በማመር ወደ በጎ ነገር መመለስ ልብ መግዘት ይመስለኛል፡፡

ዛሬ አለማችንን በአንድነት እያሰጨነቀ ያለው መድሃኒት አልባ ወረርሽኝ የብዙ ሰዎችን ህይወት እየቀጠፋ መሆኑን በአይናችን እያየን እንዳለየን እየሰማን እንዳልሰማን ያደረገን ልብ ያለመግዛት ይመስላል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት እንደየእምነታቸው ወደ ፈጣሪ በሚጮሁበትና ሚዲያዎች ስለበሰሽታው አስከፊነት ሌት ተቀን በሚናገሩበት በአሁኑ ሰአት ተስብሰቦ ሺሻ ማጨስ እና ተመሳሳይ ድርጊቶች መፈጸም ልብ ያለመግዛት ነው፡፡

ለመሆኑ ለዚህ ገዳይ ወረርሽኝ ትኩረት እንዳንሰጥ ያደረገን ምን ይሆን? የልብ ገቢያውስ ወዴት ነው?

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top