Connect with us

ትምህርት ሚኒስቴር የግል ት/ቤቶችን ክፍያ በተመለከተ መመሪያ አወጣ

ትምህርት ሚኒስቴር የግል ት/ቤቶችን ክፍያ በተመለከተ መመሪያ አወጣ
Photo: Solomon Yimer

ወንጀል ነክ

ትምህርት ሚኒስቴር የግል ት/ቤቶችን ክፍያ በተመለከተ መመሪያ አወጣ

ትምህርት ሚኒስቴር የግል ት/ቤቶችን ክፍያ በተመለከተ መመሪያ አወጣ

የግል ትምህርት ቤቶች ቴክኖሎጂን በመጠቀም ተማሪዎችን እንዲያግዙና የክፍያ ሁኔታን ከወላጆች ጋር ተመካክረው እንዲወስኑ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በኮሮና ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ተከትሎ በግል ትምህርት ቤቶች አካባቢ ስለሚኖረው የተማሪ ትምህርት ቤት፣ የተማሪ ወላጆችና የመምህራን ትምህርት ቤት ግንኙነትን የተመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮችን የዳሰሰ መመሪያ አስተላልፏል፡፡

ወቅታዊ ችግርን በመተሳሰብና በመተጋገዝ ማለፍ እንደሚገባ ያሳሰበው ትምህርት ሚኒስቴር ከክፍያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሊፈቱ የሚችሉባቸውን ሁኔታዎችም አመላክቷል፡፡ የግል ትምህርት ቤቶች የሠራተኞቻቸውን ደመወዝ ክፍያ ማቋረጥ እንደሌለባቸው ያሳሰበው ሚኒስቴሩ የተማሪዎች የትምህርት ክፍያን በተመለከተ የወላጆች ኮሚቴና የትምህርት ቤቶች መሪዎች እየተመካከሩ እንዲወስኑ አመላክቷል፡፡

ወላጆች በረዥም ጊዜ እንዲከፍሉ፣ አቅማቸው ያልፈቀደ በግማሽ እንዲከፍሉና ምንም አቅም የሌላቸው ደግሞ ይቅርታ እንዲደረግላቸው የሚኒስቴሩ ማብራሪያ አመላክቷል፡፡ ወላጆች ከ50 እስከ 75 በመቶ የመክፈል ግዴታ የተጣለባቸው ሲሆን ትምህርት ቤቶች ደግሞ በቴሌግራም አማካኝነት የመገናኛ አውታር ዘርግተው ለተማሪዎች እገዛ የማድረግ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡

(ምንጭ አማራ መገናኛ ብዙሀን ድርጅት)

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top