Connect with us

‹‹ስቴይ ሆም›› የሚለው አዋጅ ፈተና የሆነባቸው ላጤዎች

‹‹ስቴይ ሆም›› የሚለው አዋጅ ፈተና የሆነባቸው ላጤዎች

መዝናኛ

‹‹ስቴይ ሆም›› የሚለው አዋጅ ፈተና የሆነባቸው ላጤዎች

‹‹ስቴይ ሆም›› የሚለው አዋጅ ፈተና የሆነባቸው ላጤዎች | (አሳዬ ደርቤ በድሬቲዩብ)

የዓለም የጤና ድርጅት ‹‹የኮሮናን ጥቃት ለመቋቋም ቤታችንን ከመዝጋት ባለፈ ልዩ ልዩ ምግቦችን በመብላትና ስፖርት በመስራት በሽታን የመከላከል አቅማችንን ማጎልበት እንደሚገባን ይመክራል፡፡

ለምሳሌ ያህል ከእኔ ቤት ቀጥሎ ያለውን ባለአንድ ክፍል ስቲድዮ የተከራየው ጎረምሳ ብንመለከት… ከወንደላጤነቱ በተጨማሪ በአለሌነቱ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም ባሕሪው ‹‹የኮሮና መቅሰፍት አምጥቶብናል›› በማለት የብሎካችን አባወራዎች ሲከሱት፣ ሴቶቹ ግን ‹‹ከቻይና በመጣ በሽታ እሱን ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አይደለም›› በማለት ይከራከሩለታል፡፡

እንዲህ ያለ ከባድ ዘመን ሲከሰት ሱባኤ እንደመግባት ‹‹ኮንዶም አምራች ድርጅቶች ጓንት ማምረት ከጀመሩ ወደፊት የላስቲክ እጥረት ሊያጋጥም ይችላል›› በሚል ግምት ቤቱን የDKT Ethiopia ምርት ማከማቻ መገዘን ማድረጉ ነው፡፡

ይሄን አደገኛ ወንደላጤ የብሎካችን ሴቶች ‹‹እንደ እሱ ሴት የሚወድ ወንድ አይተን አናውቅም›› እያሉ ያወሩለታል፡፡ እኔ ግን ‹‹እንደሱ ሴት የሚጠላ ሰው ዐይቼ አላውቅም›› እላለሁ፡፡ ምክንያቱም በየሳምንቱ በግ እያረዴ የሚበላ ሰው ‹‹ሥጋ ይወዳል እንጂ በግ ይወዳል›› ተብሎ ሊገለጽ እንደማይችል ሁሉ፣ በየጊዜው አዲስ ሴት እየጠበሰ ገላቸውን ከተጠቀመ በኋላ ‹‹ዐይንሽን ለአፈር›› የሚል ጎረምሣም ‹‹ግብረ ሥጋ እንጂ ሴት ይወዳል›› ሊባል አይችልም፡፡

የሆነው ሆኖ ግን ጎረቤቴ አሁንም ቢሆን ውሜናይዘር ዓመሉን ትቶ ሳኒታይዘር እየተጠቀመ ይሄን አስቸጋሪ ጊዜ የማለፍ ፍላጎት የለውም፡፡ ስለሆነም ቀኑን ሙሉ ኮሪደር ላይ እየተንጎራደዴ ከሚደውልላቸው ሴቶች መሃከል ስብከቱን አምና የምትመጣ ኮረዳ ማግኘት ባይችልም እሱ ግን ጥረቱን አልተወም፡፡ ይልቅስ ፊቱን በማስክ ሸፍኖ እና ሞባይሉን ጆሮው ላይ ደግኖ ወደ ደጅ ይወጣና ‹‹ኮሮና ደግሞ ምኑ ያስፈራል? ጉንፋን እኮ ነው›› እያለ ስልክ ቁጥር የተቀበላቸውን ሴቶች ሁሉ በየተራ ሲጀነጅን ነው የከረመው፡፡

ሆኖም ግን ይሄ ልፋቱ ካርዱንና ጊዜውን ከመጨረስ ባለፈ ፋይዳ እንደሌለው ባወቀ ጊዜ ስልኩን ጥሎ ብሎኩ ላይ ማንዣበብ ስለጀመረ… በረዶ ጠባሽ ምላሱን የምናውቅ አባወራዎች ሁሉ ኮሮናን ትተን ሚስቶቻችንን ለመጠበቅ ተገደድን፡፡

ከሶስት ቀን በፊት ታዲያ ወደ ሱቅ በመሄድ አንዳንድ አስቤዛዎችን ሸምቼ ስመለስ ይህ ውርጋጥ ባላሰብኩት መንገድ ተከስቶ ህጻን ትይዝልን ዘንድ በስንት ደላላ አፈላልገን የቀጠርናትን ኮረዳ የልጆች ልብስ ልታለቀልቅ እንደወጣች ኮሪደር ላይ በቁጥጥር ስር አውሏት አገኘሁ፡፡ በጅንጀኛው ልቧን ያተነሳችው ኮረዳም የኦሞ አረፋ በሞላው ገንዳ ውስጥ ልብስ ሳታስገባ ውሃውን ብቻ እያንቧጨረቀችና እየጠመዘዘች ፈገግ ብላ ስታዳምጠው አየሁ፡፡ ይሄንንም ስመለከት በንዴት እየተንደረደርኩ ‹‹ክብርህን ብትጠብቅ ምን አለበት?›› ብዬ ስናገረው ‹‹አንተ ደግሞ እርቀትህን ጠብቅ›› ብሎኝ ወደ ቤቱ ገባ፡፡

ከዚያች ቅጽበት አንስቶም እንደ ቤተሰብ አባል የምንቆጥራት ሠራተኛችን ልብስ ልታጥብ ወጥታ ልቧን ጥላ ስለገባች ጓዳውም ሆነ ሥራው አስጠልቷት አረፈ፡፡ በመሆኑም ምን ብሎ እንዳሰመጣት ባናውቅም ‹‹ጓዳ ግቢና ሽንኩርት ክተፊልኝ›› ስትባል ‹‹ዐይኔን እንዳያቃጥለኝ ኮሪደር ላይ ሆኜ ነው የምከትፈው›› ማለት ጀመረች፡፡

ባለቤቴ ‹‹ሳሎኑን ወልውይውኝ›› ስትላት ደግሞ ‹‹ማስክና ጓንት ግዢልኝ›› ከማለቷም በላይ በስንት ፍለጋ ለእጃችን በገዛነው ሳኒታይዘር ሳሎኑን ስትወለውል ተገኘች፡፡ ያም ሆኖ ግን በዚህ ሰዓት ሠራተኛ ማግኘት ከባድ መሆኑን በመረዳት የተቆጣት ሰው አልነበረም ነበር፡፡

ዛሬ እረፋድ ላይ ታዲያ እሜቴ ምግብ ለመሥራት አስባ ‹‹ይቺን ልጅ’ማ እንኪ ተቀበይኝ›› ስትላት ‹‹አካላዊ ንክኪ ተከልክሏል›› በማለት መለሰችላት፡፡

‹‹እና እንዴት አድርገሽ ነው የምትይዢልኝ?›› ተብላ በተጠየቀች ጊዜም ‹‹እርቀቴን ጠብቄ እይዝልሻለሁ›› ብላት ሁለት እርምጃ ከተራመደች በኋላ ከወንደላጤው ቤት ገባች፡፡

በዚህም ድርጊቷ የተበሳጨችው ባለቤቴ ተከትላት በመሄድ ‹‹ልጅ የሚታቀፍልኝ ሰው እንደሌለኝ እያወቅሽ እንዴት ይሄንን ታደርጊያለሽ?›› በማለት ስትጮህባት የሠጠቻት መልስ የሚከተለውን ነበር፡፡
‹‹ባለቤትሽ አስተቃቀፍ ያውቅ የለም እንዴ? ለምን እሱ አያግዝሽም!››

Click to comment

More in መዝናኛ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top