Connect with us

የኮሮና ቫይረስ በድሬደዋ

የኮሮና ቫይረስ በድሬደዋ
Photo: Social media

ዜና

የኮሮና ቫይረስ በድሬደዋ

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስን የተመለከተ ትላንት ለጋዜጠኞች መግለጫ ተሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት በዛሬው እለት ስራቸውን የጀመሩት አዲሷ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ናቸው።

ኃላፊዋ በመግለጫው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች:-

– በድሬዳዋ አስተዳደር እስከዛሬ ድረስ የኮሮና ቫይረስ ምልክት ከታየባቸው 9 ሰዎች ላይ በተወሰደ ናሙና 2 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል::

– ከሁለቱም ግለሰቦች ጋር የቅርብ ንክኪ እንዳላቸው የታወቀ 19 ግለሰቦች የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት ወይም በተለምዶ ፈርንሳይ በሚባለው ሆስፒታል ተለይተው እንዲቆዩ ተደርጏል።

– ከግለሰቦቹ ጋር ንክኪ ይኖራቸዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ተጨማሪ ግለሰቦችን በመለየት እና ወደ ለይቶ ማቆያ ለማስገባት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ይገኛል።

– በተጨማሪም ከግለሰቦቹ ጋር ንክኪ ሊኖረኝ ይችላል ብለው የሚገምቱ ወይም የሚጠራጠሩ ግለሰቦች ለራሳቸውም ሆነ ለህብረተሰቡ ደህንነት ሲሉ ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ውስጥ በመሆን ማህበረሰባዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት ይገባቸዋል።

– በድሬዳዋ አስተዳደር በቀጣይ 2 ሳምንት ውስጥ በቫይረሱ የሚያዙ ግለሰቦች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ማሳያዎች አሉ።

– በመሆኑም መላው የአስተዳደሩ ነዋሪ በቀጣይ 2 ሳምንታት ከቤት ባለመውጣት እና እራሱን ከሰዎች ንክኪ በማራቅ እንዲሁም አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን በማድረግ በሽታውን መከላከል ይገባዋል።

ምንጭ፦ DMMA

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top