Connect with us

የጊዜ ቀጠሮ እስረኞች ከእስር ሊለቀቁ ይገባል

የጊዜ ቀጠሮ እስረኞች ከእስር ሊለቀቁ ይገባል
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

የጊዜ ቀጠሮ እስረኞች ከእስር ሊለቀቁ ይገባል

የጊዜ ቀጠሮ እስረኞች ከእስር ሊለቀቁ ይገባል
(ሙሉጌታ በላይ)

ህግ በእኩልነት በፍትሀዊነት ሊፈፀም ይገባል። ሁሌም እንደምለው በእኩልነት እና በፍትሀዊነት ከማይፈፀም ህግ ይልቅ አፋኝ ህግ ይበልጥ ህጋዊ ነው።

የኮሮና ቫይረስ ሊስከትለው ከሚችለው ጉዳት አኳያ ወንጀል ሰርተዋል ተብለው በህግ ሂደት ወንጀለኛ ተብለው የተፈረደባቸው ሰዎች በይቅርታ ወጥተዎል። በተለያየ ምክንያት ክሳቸው የተቋረጠላቸው በርካታ ሰዎች ከእስር ተለቀዎል ።

አዎ በማረሚያቤት ካለው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር አኳያ ምክንያታዊ ውሳኔ ነው ከነችግሩ።

ነገር ግን ለሁለተኛ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ጉዳያቸው ሳይታይ የተራዘመባቸው፤ በህግ ፊት ወንጀለኝነታቸው እስኪረጋገጥ ንፁህ ሆነው የመቆጠር ብሎም ጉዳያቸው በአጭር ጊዜ እንዲታይላቸው መብት ያላቸው የጊዜ ቀጠሮ እስረኞች ለምን ከሀገር እንዳይወጡ ታግደው በቂ ዎስ ጠርተው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ አልተደረገም? ከቤታቸው እንዳይወጡ ከወጡ መልሰው እንዲገቡ የማድረግ አሰራርም መከተል ይቻላል።

ቀድሞም ዎስትና ተከልክለው በተራዘመ ቀጠሮ ጉዳያቸው ሳያልቅ ወራት እና አመታትን ያስቆጠሩ እስረኞች በዎስ ቢወጡ ከወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታና ጉዳያቸው ሳይታይ ሊቆይ ከሚችልበት ጊዜ ርዝማኔ አኳያ ተገቢ ይመስለኛል ።

ባጠረ ጊዜ ችግሩ ተቀርፎ ጉዳያቸው መታየት ቢጀመር እንኳ በተደጋጋሚ ጊዜ ቀጠሮዎች የተቀየሩ በመሆኑ የአንዱ ጉዳይ በሌላው ላይ የተደራረበ በመሆኑ ጉዳያቸው በአጭር ጊዜ እንደማያልቅ ግልፅ ነው።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top