Connect with us

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ እየተሰራጩ ለሚገኙ ሀሰተኛ መረጃዎች ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ተገለጸ

በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ እየተሰራጩ ለሚገኙ ሀሰተኛ መረጃዎች ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ተገለጸ
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ እየተሰራጩ ለሚገኙ ሀሰተኛ መረጃዎች ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ተገለጸ

በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ እየተሰራጩ ለሚገኙ ሀሰተኛ መረጃዎች ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ተገለጸ

የኮቪድ-19 በሽታ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን የተመለከቱ እውነትን መሠረት ያላደረጉ ሀሰተኛ ዘገባዎች ህጋዊ ካልሆኑ አካላት በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገጾች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ፡፡

የኮቪድ-19 በሽታ ሥርጭትን የተመለከቱ ሀሰተኛ መረጃዎች ሰዎች ስለበሽታው የተዛባ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ለተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቃቶች ተጋላጭ እንዲሆኑ እያደረገ ይገኛል፡፡ ጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ጨምሮ የተለያዩ ክፍተኛ የመንግስት አካላትም ትኩረት የሚያስፈልገው መሆኑን እየገለጹ ነው፡፡

የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ አሁን ላይ በሽታውን ብቻ ሳይሆን ስለ በሽታው የሚወራውን ሀሰተኛ መረጃ እየተዋጋን ነው ሲሉ አሳሳቢነቱን ገልጸዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት በበኩሉ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ባወጣው መግለጫ በህዝብ ጤናና ደህንነት ላይ በተለያዩ መንገዶች ሽብር በሚነዙ አካላት ላይ የሕግ አስከባሪ አካላት ሕግ የማስከበር ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ ትዕዛዝ አስተላልፉል፡፡

የጤና ሚኒስቴር በበኩሉ ህብረተሰቡ በተለይም በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች ላይ ከሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች ሊጠነቀቅ እንደሚገባ በተደጋጋሚ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንም ቫይረሱን በተመለከተ ህብረተሰቡን የሚያደናግሩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰድ መጀመሩን ገልጿል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ባወጣው መግለጫም የቫይረሱን ስርጭት በተመለከተ ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ህዝብን የሚያሸብሩ አካላት ከህገ-ወጥ ተግባራቸው እንዲታቀቡ በማስጠንቀቅ ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ በሚወሰዱ ህጋዊ እርምጃዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንት ኤጀንሲ በበኩሉ ህብረተሰቡ ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ባልተናነሰ መልኩ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች አማካኝነት በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገር ደረጃ በሚሰራጩ የሀሰት መረጃዎች ሰለባ እንዳይሆን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ይመክራል፡፡

የበሽታውን ስርጭት ግምት ውስጥ በማስገባት የመከላከያ መንገዶችን እና ከመንግስት የሚተላለፉ ማሳሰቢያዎች ላይ ትኩረት በመስጠት ህብረተሰቡ ትክክለኛውን መረጃ እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን ለበጎ ተግባር እንዲጠቀሙበት ያሳስባል፡፡

ምንጭ:- ኢመደኤ | Information Network Security Agency

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top