Connect with us

ከኢትዮጵያውያን ጎን መቆም መገለጫዎ ለኾነው ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን እናመሰግናለን

በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ከኢትዮጵያውያን ጎን መቆም መገለጫዎ ለኾነው ክቡር ዶክተር ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን እናመሰግናለን፡
Photo: Social media

አስገራሚ

ከኢትዮጵያውያን ጎን መቆም መገለጫዎ ለኾነው ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን እናመሰግናለን

በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ከኢትዮጵያውያን ጎን መቆም መገለጫዎ ለኾነው ክቡር ዶክተር ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን እናመሰግናለን፡፡
****
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ
በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሁሌም ከኢትዮጵያውያን ጎን አሉ፡፡ መልካም ማድረጋቸው በየዘመኑ ተወድሷል፡፡ ሀገር ከፍ ትል ዘንድ ከፍ ያሉ ሀሳቦችን ይዘው ተአምር የአሰሩ ባለሃብት ናቸው፡፡ የሰሯቸው ግዙፍ የልማት ስራዎች አልተደገሙም፡፡ እነሆ 120 ሚሊዮን ለኮሮና መከላከያ መስጠታቸውን ሰማሁ፡፡ ምን ያለ የታደለ መንፈስ ነው አልኩ ለራሴ፡፡

ሀገር እንዲህ በኢንቨስትመንት ምቹ ሳትሆን፤ ሰዎቹ ከጫካ ነው የመጡት አይታመኑም በሚል ብር ያለው ነገ እንይ ብሎ ባደፈጠበት፣ በጦርነት በደቀቀች ሀገር ልማት ብለው ደፍረው ማልማትን ፈር የቀደዱ ባለሃብት ናቸው፡፡

ከዚያ በኋላ የምንወዳቸውን ሰዎች ሁሉ ታድገዋል፡፡ የምንወዳቸውን እሴቶች አኑረዋል፡፡ በሀገረ ሲውዲን እንዴት ያሉ ክቡር አልሚ መሆናቸውን ሳይ ከስማቸው ጋር አብሮ ለሚነሱ ችግሮች በሙሉ ተጠያቂው እኛ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ ተረድቻለሁ፡፡

በስውዲን የግዙፍ ኢንቨስትመንቶቻቸውን ፍሬ በዓይኔ አይቻለሁ፡፡ ስውዲናውያን የሚያብሯቸው ትልቅ ባለሃብት መሆናቸውን ተገንዝቤያለሁ፡፡ የግብጽ ጋዜጦች ሰውዬው በሳውዲ አረብያ በታሰሩበት ወቅት የህዳሴው ግድብ የዶላር ምንጭ መድረቁን መዘገባቸውን አንብበን እንኳን ያጎደሉትን በመርሳት የሞሉትን ለማወደስ ያልቻልን ነን፡፡

ሀገር ስትጣራ ብዙ ጊዜ አድምቀው አቤት ብለዋል፡፡ ለብዙ ሺህዎች የስራ እድል የፈጠረ ሀብት አፍሰዋል፡፡ የምናከብራቸውን አክብረው ከፍ አድረገዋል፡፡ ከወገን ጎን የቆሙበት የታሪክ ምዕራፍ ብዙ ነው፡፡ ብዙ የአደባባይ ሀቅ ስለሆነ አላወራውም፡፡

ዛሬ የግዙፍ ኢንዱስትሪዎቻቸው ቱሩፋት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች ናቸው፡፡ እንደ ሻራተን ያሉ ሀብቶቻቸው ብርቅ ቅርስ ሆነው ቀርተዋል፡፡ እንደ ሚሊኒየም አዳራሽ ያሉት ጊዜያዊ እሴታቸው ቋሚ ኾኖ ዛሬም ለቆመው ሰው እያገለገለ ነው፡፡

ያሉበትን ሁኔታ አላውቅም፡፡ በምንም ሁኔታ ውስጥ ግን ከኢትዮጵያውያን ጎን መቆማቸውን አሳይተዋል፡፡ የሩቂያ ልጅ፣ ሼኹ፣ ኢትዮጵያዊው፣ ሼህ መሃመድ ሁሴን አላሙዲን እናመሰግናለን፡፡ የሚወደን ሊያተርፍብን በሚያደባበት በዚህ ደመና ውስጥ 120 ሚሊዮን ብር በማይተመን ሀገር የመውደድ ስሜት እንካችሁ ብለዋልና፤

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አስገራሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top