Connect with us

የቡድን 20 አባል ሀገራት 5 ትሪሊዮን ዶላር ለመልቀቅ ቃል ገቡ

የቡድን 20 አባል ሀገራት 5 ትሪሊዮን ዶላር ለመልቀቅ ቃል ገቡ
Photo Facebook

ኢኮኖሚ

የቡድን 20 አባል ሀገራት 5 ትሪሊዮን ዶላር ለመልቀቅ ቃል ገቡ

የወቅቱ የቡድን 20 አባል ሀገራት ሊቀመንበር ሳውዲ አረቢያ ያዘጋጀችው የአባል ሀገራቱ የቪዲዮ ኮንፈረንስ የተጠናቀቀ ሲሆን ያንን ተከትሎም አባል ሀገራቱ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

አባል ሀገራቱ በመግለጫቸው ኮሮና ቫይረስ እያደረሰ ያለውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የፋይናንስ ጉዳት ለመቋቋም 5 ትሪሊዮን ዶላር ወደ ዓለም ገበያ ፈሰስ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

አባል ሀገራቱ ከዓለም የገንዝብ ድርጅት (አይኤምኤፍ)፣ ከዓለም የጤና ድርጅት እና ከአህጉራዊ ባንኮች ጋር ሆነው የፋይናንስ ማዕቀፍ በማዘጋጀት በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ለመደገፍ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

የቡድን 20 አባል ሀገራቱ በጋራ መግለጫቸው በአንድነት በመሆን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመግታት እንደሚሰሩም አመልክተዋል።

ችግሩን ለመከላከል የተቀናጀ ዓለም አቀፋዊ ምላሽ እንደሚያስፈልግም አስምረውበታል።(ኢቲቪ)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top