Connect with us

በየክፍለ ከተማው ጊዜያዊ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ማእከላት እንዲዘጋጁ ተወሰነ

በየክፍለ ከተማው ጊዜያዊ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ማእከላት እንዲዘጋጁ ተወሰነ
Photo Facebook

ዜና

በየክፍለ ከተማው ጊዜያዊ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ማእከላት እንዲዘጋጁ ተወሰነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከክፍለ-ከተማ ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ኮሮና ቫይረስን ከመከላከል እና ፀጥታን ከማስከበር ጋር በተያያዘ በየክፍለ ከተማው እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ኢ/ር ታከለ በዚሁ ጊዜ በየክፍለ ከተማው ጊዜያዊ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ማእከላት በአፋጣኝ እንዲዘጋጁ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ በየክፍለ ከተማው ጠንካራ ቁጥጥር እንዲደረግ እና ሕጉን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ለክፍለ ከተማ ሥራ አስፈጻሚዎች መመሪያ ሰጥተዋል።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ግንዛቤ የማስጨበጥ እና ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራዎች በተቀናጀ መልኩ እንዲከናወኑም አሳስበዋል።

ምንጭ፡- የከንቲባ ጽ/ቤት

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top