Connect with us

የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ሲያደርጉ በተገኙ 83 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ሲያደርጉ በተገኙ 83 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
Photo : Facebook

ህግና ስርዓት

የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ሲያደርጉ በተገኙ 83 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ዋጋን በጋራ በመወሰን ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ንረት እንዲፈጠርና በነዋሪው ላይ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ሲያደርጉ በተገኙ 83 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ችግሩን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ግብረ ሀይል አስታውቋል።

ግብረ ሀይሉ በዛሬው እለት ባካሄደው ክትትልና ቁጥጥር በዚህ አስቸጋሪ ወቅት አንዳንድ ስግብግ ነጋዴዎች የንግድ አሰራሩን በመጣስ፣ ምርት በማከማቸትና በመደበቅ ሰው ሰራሽ እጥረት እንዲፈጠር በማድረግ ላይ መሆናቸውን ማረጋገጡን ገልጿል፡፡

ይህንንም ለመከላከል ግብረ ሀይሉ ያለደረሰኝ ግብይት በማካሄድ እንዲሁም ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ዋጋን በጋራ በመወሰን ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ንረት እንዲፈጠር እና በነዋሪው ላይ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ሲያደርጉ በተገኙ 83 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ግብረ ሀይሉ እርምጃውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማስጠንቀቁንም ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪ ጽ/ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

በአገራችን የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ በከተማችን ተገቢ ያልሆነ የምርቶች ዋጋ ጭማሪ እንዳይፈጠር ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚዘልቅ ግብረ ሀይል መቋቋሙ ይታወሳል፡፡

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top