Connect with us

የወረቀት ላይ ፈተና እድሜ እንደማይኖረው ተገለጸ

የወረቀት ላይ ፈተና እድሜ እንደማይኖረው ተገለጸ

ወንጀል ነክ

የወረቀት ላይ ፈተና እድሜ እንደማይኖረው ተገለጸ

ከተያዘው ዓመት ጀምሮ የወረቀት ፈተና እድሜ እንደማይኖረውና ማርክ አስተካክሉልኝ የሚል ጥያቄም ቦታ እንደሚያጣ የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሔር ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት በፈተና ዙሪያ እርማት ፣ ፈተናውን ማስተዳደር፣ መፈተንና ውጤት አገላለጽ ድረስ ያሉ ሂደቶችን ዘመናዊ በማድረግ በአገር አቀፍ ደረጃ የወረቀት ፈተና እድሜ እንደሚያጥር ገልፀዋል።

ፈተናን በአይፓድ መፈተን እንደምንችል ያረጋገጥንበት ወቅት ላይ ነን ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በእርግጥ ከጀርባው ሊሟሉ የሚገባቸው በርካታ ነገሮች ቢኖሩም አሁን ላይ በኤጀንሲው በኩል ሙሉ ዝግጁነት ስለመኖሩም ጠቁመዋል።

ዘንድሮ 450 ሺ የሚጠጉ የ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች እንዳሉን እንገምታለን፤ መሟላት የሚገባቸው ነገሮችን አሟልተን የመንግስት ትኩረት በዚሁ ከቀጠለ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተማሪዎቹ እንዲለማመዱት በማድረግ ፈተናዎችን በላፕቶፕ ኮምፒውተርና በአይፓድ ለመስጠት እንደሚቻል ተናግረዋል።

በሌላ በኩልም ባለፉት ዓመታት ኤጀንሲው በተለያየ ደረጃ እድገት አሳይቷል፤ ትልቁ ውጤቱም አገልግሎቱን ‘አውቶሜት’ ለማድረግ እያካሄደ ያለው ስራ ነው፤ በአሁኑ ወቅት ለዘመናት በኤጀንሲው በወረቀት ተቀምጠው የነበሩ የትምህርት መረጃዎች ተደራጅተው በአውቶሜሽን እንዲቀመጡ ሆኗል። ከዚህ አንጻር ማንኛውም ሰው ወደ ኋላ ሄዶ መረጃን ሲጠይቅ በአጭር ጊዜ ውስጥ የትምህርት መረጃውን የሚያገኝበት ሁኔታ ተመቻችቷል።

አዲስ ዘመን የካቲት 18/2012

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top