Connect with us

ለባልሽ ንገሪው-ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገር እንዳየሽው ልክ እንደ አንቺ በስስት እንደምታየው

ለባልሽ ንገሪው-ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገር እንዳየሽው ልክ እንደ አንቺ በስስት እንደምታየው፤
Photo: amleset muchie

መዝናኛ

ለባልሽ ንገሪው-ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገር እንዳየሽው ልክ እንደ አንቺ በስስት እንደምታየው

ለባልሽ ንገሪው-ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገር እንዳየሽው ልክ እንደ አንቺ በስስት እንደምታየው፤
****
ከሄኖክ ስዩም

ሰውዬው ዝም ብሎ ሙዚቀኛ አይደለም፡፡ የስዕለት ልጅ ነው፤ ሀገር እንዲህ ያለው ሲያምራት “ምነው በሰጠህኝና በሰጠሁህ” የምትለው፤ እንዲህ ኾኖ የተሰጠ ይመስለኛል፡፡

ሀገር ትሳሳለታለች፤ ዛሬም ሰውዬው ሳይኾን ልጁ ነው፡፡ ዛሬም አባወራው ብላቴና፣ ዛሬም ሙሉ ስሙ አምስት ፊደል ረዝሞብን በሁለት ፊደል የምንጠራው ተቆላማጭ ዛሬም ቴዲ፤

ስም ተግባር ይመራል፡፡ እርሱ እንደ ቴዎድሮስ ነው፡፡ የተበተነ ሀሳብ ለመሰብሰብ የደከመ፤ ከዘመነ መሣፍንት በሚከፋ የልዩነት ዘመን ብቅ ብሎ በጥበብ ከጫፍ ጫፍ ያስገበረ፤ የልዩነት ከያኒያን በየጎጣቸው በመሰፈኑበት ዘመን ተፈጥሮ በብሔራዊ ስሜት የሀገር ዘውድ የደፋ፤ እሱ ንጉሥ ነው፡፡

ይሄንን ሁሉ የማስበው ከአባቶቻችን የነጻነት ዋጋ ባድማ ላይ ኾኜ ነው፡፡ ጊዶሌ ነኝ፡፡ የጋርዱላን ሞገስ ሽቅብ እያየሁ፤ በዚህ መካከል አንድ ፎቶ አየሁ፡፡ የአንድ ጀግና ሰው ሚስት ብቻ አይደለችም፤ አንዲት ጀግና ሴትም እንጂ፤ ስለ አፈርና ተፈጥሮ ግድ ብሏት የደከመች ጥበበኛ፤ አምለሰት ሙጬ

የፎቶው መግለጫ እሷ የባሏን የሙዚቃ ድግስ ከ150 ሺህ ህዝብ ጋር ሆና እያየች ነው፤፤ ከፍ ሲል ልቧም አብሮ ከፍ በሚልበት ቅጽበት አንድ ንስር በንስር ዓይን አይቶ ያስቀረው ፎቶ ነው፡፡ ባሏን በስስት ታየዋለች፡፡ በዚያ እይታ ውስጥ የሀገር ዓይን እንዲህ እንደሚሆን አሰብሁ፤

የት አግኝቼ ልንገራት ይሆን አልሁ ለራሴ፤ ከዚያም ጻፍኩላት፤ ወይ ታነበዋለች፤ ወይ ያነበበ ይነግራታል፤ ወይ ባታነበው ካለመጻፍ ይሻላል፡፡

“ይኼውልሽ አምለሰት፤ እንዴት አድርገሽ ነው የምታየው በይ፤ በሚስት አይን የእናት እይታ፤ እንዲህ ያለ ስስት፤ ይልቅ ለባልሽ ንገሪው እሺ፤ እንዲህ በይው የአንቺን ፎቶ አሳይውና፣ በጣቶችሽ እየጠቆምሽ፤
ያ ሰው እንዳለህ…

ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገር እንዳየሽው ልክ እንዳንቺ በስስት ነው የምታየው” አለኝ በይው፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in መዝናኛ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top