Connect with us

ታከለ ኡማ በቦሌ ክፍለከተማ ሰዎች የተገደሉበት ክስተት በጋራ ኮምቴ እንዲጣራ ተስማሙ

ታከለ ኡማ በቦሌ ክፍለከተማ ሰዎች የተገደሉበት ክስተት በጋራ ኮምቴ እንዲጣራ ተስማሙ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ታከለ ኡማ በቦሌ ክፍለከተማ ሰዎች የተገደሉበት ክስተት በጋራ ኮምቴ እንዲጣራ ተስማሙ

የአዲስአበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር ተወያይተው ችግሩ ከሦስት አካላት በተውጣጣ ኮሚቴ እንዲጣራ ተስማሙ

ምክትል ከንቲባው የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ 24 በሚባለው አካባቢ ተፈጥሮ የነበረውን ችግር በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ጋር ተወያይተው ችግሩ ከሦስት አካላት በተውጣጣ ኮሚቴ እንዲጣራ ተስማምተዋል።

ከሦስት አካላት ማለትም ከቤተ ክርስቲያን፣ ከአካባቢው ሽማግሌዎች እና ከመንግሥት አካል የተቋቋመው ኮሚቴ በዐሥር ቀናት ውስጥ ችግር የፈጠሩትን አካላት ማንነት፣ በቦታው የነበረውን ንዋያተ ቅድሳት ሁኔታ እንዲሁም ስለቦታው በዝርዝር አጥንቶ እንዲያቀርብ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በተፈጠረው ችግር ምክንያት ታስረው የነበሩ ክርስቲያኖች ክሳቸው ተቋርጦ እንደሚፈቱም ከንቲባው ለቋሚ ሲኖዶስ አባላት አረጋግጠዋል።(ማህበረ ቅዱሳን)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top