Connect with us

ለታሪክ ትምህርት ማስተማሪያነት የተዘጋጀው ሞጁል የተለያዩ የዘርፉ ምሁራንን አስተያየቶች አካትቶ ለማስተማሪያነት ዝግጁ ሆነ

ለታሪክ ትምህርት ማስተማሪያነት የተዘጋጀው ሞጁል የተለያዩ የዘርፉ ምሁራንን አስተያየቶች አካትቶ ለማስተማሪያነት ዝግጁ ሆነ
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

ለታሪክ ትምህርት ማስተማሪያነት የተዘጋጀው ሞጁል የተለያዩ የዘርፉ ምሁራንን አስተያየቶች አካትቶ ለማስተማሪያነት ዝግጁ ሆነ

የኢትዮጵያና የአፍሪካ ቀንድ ታሪክ ማስተማሪያ ሞጁል ቫሊዲሽን ወርክሾፕ ትላንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በወርክሾፑ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም የታሪክ ትምህርት ከቀደመው ህዝብ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነልቦናዊ ገፅታዎችን በመረዳት ከቀደመው ትውልድ ከስኬቱም ከውድቀቱም፣ ከድሉም ከሽንፈቱም፣ ከጥንካሬውም ከድክመቱም፣ ከመልካሙም ከመጥፎውም፣ ለዛሬ ህላዊ ለነገም ትልም ጠቃሚ ትምህርት የሚወሰድበት ሲሆን ይህም በራስ መተማመን የመንፈስ ጥንካሬና ኩራት ይሰጣል ብለዋል፡፡

ፕሮፌሰር ሂሩት እንዳሉት ኢትዮጵያ የእድሜ ባለጸጋ አገር እንደመሆኗ ብዙ መማሪያ ሊሆን የሚችል ታሪክ አላት፡፡ የታሪክ ትምህርት የምናስተምርበት ዋነኛ ምክንያት ቀሪው ትውልድ ከስህተቶች ተምሮ ራሱን እንዲያርም ለማስቻል እንደመሆኑ የምንግባባበትና የሚጠቅመንን ለይተን መያዝ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሞጁሉ ከሲለብስ ዝግጅት ጀምሮ የተለያዩ ሂደቶችን አልፎ ለዛሬ ደርሷል ያሉት ሚኒስትሯ በዘርፉ ምሁራን ጠለቅ ያሉ አስተያየቶች ተሰጥቶበታል ብለዋል።
በረቂቅ ሰነዱ ላይ በአርታኢዎቹና በሌሎች አሰተያየት ሰጪዎች በተሰጠው ግብዓት መሰረት በርካታ ማሻሻያዎች እና እርማት የተደረገበት ሲሆን በዛሬው ውይይት ከተሳታፊዎች የተነሱ ግብዓቶችን በማካተት በአገራችን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ታሪክን ለማስተማር የሚያስችል ሞጁል ይወጣል ብለዋል፡፡

ከሞጁሉ ዝግጅት በኃላ አርትኦት የሰራው ቡድን አባል አቶ ካሱ ጡሚሶ እንዳሉት የመጀመሪያው ሞጁል በ7 ምዕራፍ የተከፋፈለ እና 107 ርዕሶችን የያዘ ሆኖ በያዝነው ዓመት ህዳር ወር ላይ ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለአስተያየት ተልኮ እንደነበርና ታህሳስ ወር ላይ ደግሞ ይሄንኑ አስተያየቶች ለማጠናቀር የሚረዳ ወርክሾፕ መካሄዱን ገልጸው አሁንም ሞጁሉ በተለያዩ ዋና ዋና የታሪክ ዘመናት የተከፋፈሉ 7 ምዕራፎችን በውስጡ ይዟል ብለዋል፡፡

አቶ ካሱ እንዳሉት በመጀመሪያው ረቂቅ ሞጁል የተለዩ ችግሮች ሙሉ በሙሉ መታረማቸውንና በተለያዩ መንገዶች የተሰበሰቡ አስተያየቶችም ተካትተው ለተማሪዎቹ አቅም በሚመጥን ደረጃና ልክ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

 

በወርክሾፑ እንደተገለጸው እስካሁን በታሪክ ምሁራን ስምምነት ያልተደረሰባቸው አንዳንድ ነጥቦች በተጨማሪ ቀጣይ ጥናቶች የሚረጋገጡ ሆነው የሞጁሉ ሁለተኛ ኢዲሽን ላይ የሚካተቱ ይሆናል፡፡

በመድረኩ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበው በፕሮሬሰር ሂሩት ወ/ማርያም፣ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌና አቶ ካሱ ጡሚሶ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በወርክሾፑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ፣ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ የታሪክ ትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ የታሪክ ትምህርት ሞጁል ጸሃፊዎች፣ የታሪክ ትምህርት ገምጋሚዎች፣ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሰው ሃብትና ቴክኖሎጂ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ፣ ባህል ሚኒስቴር፣ ትምህርት ሚኒስቴር እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት ተሳትፈዋል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top