Connect with us

አሸብር ባልቻ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

አሸብር ባልቻ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ
Photo: Facebook

ዜና

አሸብር ባልቻ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

አቶ አሸብር ባልቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ በ1973 ዓ.ም. የተወለዱት አቶ አሸብር የመደመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በዚያው በአምቦ አዲስ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በአምቦ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በቀድሞ የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፤ በአሁኑ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው 1995 ዓ.ም. ላይ በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡

ከታላቋ ብሪታንያ ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ በዓለምአቀፍ ቢዝነስ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡

ከስዊዲን ሀገር ኬ. ቲ. ኤች ዩኒቨርሲቲ በዘላቂ ኢነርጂ ምህንድስና ዘርፍ ተጨማሪ ኮርሶችን ወስደዋል፡፡

አቶ አሸብር በሜካኒካል ምህንድስና ከተመረቁ በኋላ በበደሌ ቢራ ፋብሪካ ጀማሪ ሜካኒካል ኢንጂነር የስራ መደብ ላይ ለ7 ወራት አገልግለዋል፡፡

ከነሐሴ 1996 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ተቀጥረው በጊምቢ -መንዲ – አሶሳ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ስራቸውን ጀምረዋል፡፡

በተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከጥር 1997 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 2003 ዓ.ም. ድረስ መሪ መካኒካል ኢንጂነር ሆነው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎችን በመቆጣጠር ተቋሙን አገልግለዋል፡፡

ከግንቦት 2003 ዓ.ም እስከ መስከረም 2012 ዓ.ም. ድረስ የገባ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ በመሆን ካገለገሉ በኋላ ከጥቅምት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ይህን ኃላፊነት እስከተቀበሉበት ቀን ድረስ የኃይል ማመንጫዎች ግንባታ ስራ አስፈፃሚ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

አቶ አሸብር ባልቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን በተለያዩ የስራ መደቦች በባለሙያነትና በኃላፊነት ለ16 ዓመታት አገልግለው ከየካቲት 09 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙን በዋና ስራ አስፈፃሚነት እንዲመሩ በተቋሙ የሥራ አመራር ቦርድ ተሹመዋል፡፡(ምንጭ የኢት ኤሌክትሪክ ሀይል)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top