Connect with us

የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች በግማሽ ዓመት 11 ቢሊዮን ብር አተረፉ

የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች በግማሽ ዓመት 11 ቢሊዮን ብር አተረፉ

ኢኮኖሚ

የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች በግማሽ ዓመት 11 ቢሊዮን ብር አተረፉ

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ሥር በፋይናንስ ዘርፍ የሚገኙ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2012 በጀት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በጊዚያዊ የሂሳብ መረጃ መሠረት ከታክስ በፊት በድምሩ 10 ነጥብ 7 ቢሊዮን አተረፉ፡፡

ይህ አፈጻጸም የልማት ድርጅቶቹ አቅደውት ከነበረው የብር 9 ነጥብ 67 ቢሊዮን ትርፍ አንጻር ሲታይ ክንውናቸው ከዕቅዳቸው ከ11 በመቶ በላይ ብልጫ እንዳለው የድርጅቶቹ አፈጻጸም በኤጀንሲው መሰብሰቢያ አዳራሽ የካቲት 5፣6 እና 11 ቀን 2012 ዓ.ም. በተገመገመበት ወቅት ታውቋል፡፡

የግምገማ መድረኩን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገብረመስቀል እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል የመሩት ሲሆን፣የየልማት ድርጅቶቹ የቦርድ ተወካዮች፣ዋና ሥራአስፈጻሚዎች፣የማኔጅመንት አባላትና እንዲሁም የኤጀንሲው የፋይናንስ ድርጅቶች ዘርፍ ዳይሬክተር እና ባለሙያዎች በግምገማው ተሳትፈዋል፡፡

ድርጅቶቹ ይህንን ትርፍ ሊያገኙ የቻሉት የባንክና የመድን አገልግሎቶች በመስጠት በሩብ ዓመቱ ብር 34 ነጥብ 35 ቢሊዮን ገቢ ለማግኘት አቅደው ብር 36 ነጥብ 64 ቢሊዮን ወይም የዕቅዳቸውን 107 በመቶ ማግኘት በመቻላቸው ነው፡፡

ከተገኘው የብር 10 ነጥብ 71 ቢሊዮን ትርፍ ከፍተኛውን ብር 9 ነጥብ 33 ቢሊዮን ወይም ከዕቅዱ 103 በመቶ በማትረፍ ከአጠቃላዩ የዘርፉ ትርፍ አፈጻጸም 87 በመቶ ያህል ድርሻ የያዘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሆን፣በባለፈው 2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈጻጸሙን አሻሽሎ ከኪሳራ የወጣው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአጠቃላይ በስድስት ወሩ ብር 951 ነጥብ 60 ሚሊዮን ወይም የዕቅዱን 483 በመቶ ሊያተርፍ ችሏል፡፡

በዚህም ለዘርፉ አጠቃላይ ትርፍ የ9 በመቶ አስተዋጽኦ በማድረግ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ደግሞ በመንፈቅ ዓመቱ ብር 427 ነጥብ 89 ሚሊዮን ወይም የዕቅዱን 101 አትርፎ ለዘርፉ ትርፍ አፈጻጸም የ4 በመቶ ድርሻ በማበርከት ሶስተኛ ደረጃ ይዟል፡፡

በግምገማው ማጠቃለያ ላይ የፋይናንስ ድርጅቶቹ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት አፈጻጸም አበረታች በመሆኑ በቀጣዮቹ የ2012 በጀት ዓመት የትግበራ ምዕራፎች ይህንኑ አጠናክረው እንዲቀጥሉና በበጀት ዓመቱ የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አቅጣጫ ተሰጥቶ ግምገማው ተጠናቋል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top