Connect with us

30,000 የሆነው በምክንያት ነው!!!

30,000 የሆነው በምክንያት ነው!!!

ባህልና ታሪክ

30,000 የሆነው በምክንያት ነው!!!

30,000 የሆነው በምክንያት ነው!!!

(ግራዚያኒ እንደገና ጨፈጨፈን…)
(አንተነህ ይግዛው)

ከአንድ ወዳጄ ጋር በቅርቡ ወደተከፈተ የስዕል ጋለሪ ጎራ አልን፡፡
የሁለት ሰዓሊያን ስራዎች የተካተቱበትን የስዕል ኤግዚቢሽን ዞር ዞር እያልን መቃኘት ጀመርን፡፡
በእውነቱ የሚያማምሩና እጅግ የሚመስጡ ስዕሎች ነበሩ ያጋጠሙን… እየተዟዟርን መመልከታችንንና መደመማችንን ቀጠልን…

በመካከል ላይ ግን…
አንድ ቦታ ላይ ስንደርስ፣ ግራ በመጋባት እርስ በእርሳችን ተያየን – እኔና ወዳጄ፡፡
ግድግዳው ላይ ከተደረደሩት ስዕሎች መካከል፣ ርዕስ እና ቁጥር ብቻ ከግርጌው የሰፈረበት ባዶ ሸራ ተሰቅሎ ይታየናል…

“የካቲት 12” ይላል ርዕሱ፡፡

ርዕሱን እያየን ግራ ተጋባን…

ድርበብ ፈገግታ የሚታይባት አንዲት ወጣት፣ ወዳለንበት ቀረብ አለችና የጋለሪው ማናጀር መሆኗን በመጥቀስ ራሷን አስተዋወቀቺን… (ግራ መጋባታችን ገብቷታል)

“አይ ቲንክ… ይሄኛው ስዕል ትንሽ ኦድ ነገር ሆኖባችኋል…” ብላ ጀመረች፡፡
“ስዕል!?…” አልኩ በልቤ፣ የበለጠ ተገርሜ፡፡
“ሌሚ ብሪፍ ዩ…” አለችና ለረጅም ማብራሪያ ተዘጋጀች፡፡

የምትለውን ለመስማት ጓጓን…

“አይ ሆፕ… የካቲት 12 ቀን ስለተፈጸመው ታሪካዊ ክስተት የሆነ አይዲያ አላችሁ?…” ዞር ብላ አየችን፡፡

በምልክት አረጋገጥንላት፡፡

“አዝ ዩ ኖ… ፋሽስት ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ…” ብላ ጀመረችና ስለግራዚያኒ ጭፍጨፋ በረጅሙ ከተረከችልን በኋላ፣ “ይህ አርትም… በዚያች አስቃቂ ቀን የተፈጸመውን ጭፍጨፋና ግፍ አርቲስቲካሊ ሪፕረዘንት የሚያደርግ ነው!…” ስትል ደመደመች፡፡

“ማ… ማለት?… እንዴት?…” ግራ በመጋባት ወደ ባዶው ሸራ እያየሁ ጠየቅኳት፡፡

“ዳትዝ ኧ ጉድ ፖይንት!… ዩዡዋሊ የካቲት 12 ሲነሳ፣ ሜንሽን የሚደረጉት አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ብቻ ናቸው!… በዕለቱ 30 ሺህ ያህል ኢትዮጵያውያን በግፍ ተጨፍጭፈዋል… ብዙዎቻችን ግን፣ ሁለቱን ደጋግመን ስናነሳ፣ የተቀሩትን ሃያ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስምንት ኢትዮጵያውያን ኢግኖር እናደርጋቸዋለን!… ይህ ስዕልም… የተረሱትን ሪፕረዘንት ለማድረግ፣ በሰዓሊው ምጡቅ ኢማጅኔሽን የተሰራ ነው!…” አለችና ባዶውን ሸራ በተመስጥኦ ማየት ጀመረች፡፡

የበለጠ ግራ ገባኝ…

“ሸራው ግን ባዶ ነው…” ብዬ ስጀምር ጣልቃ ገብታ አቋረጠቺኝ፡፡
“ኖ!… እትስ ናት ባዶ!… ሰዓሊው ለአንተ ባዶ ከመሰለህ ሸራ ጋር፣ የኢማጅኔሽን ነጻነት አብሮ ሰጥቶናል!… ባዶ የምትለው ቦታ ላይ፣ የራስህን ኢማጅኔሽን ተጠቅመህ የተረሱትን ሰማዕታት ሪፕረዘንት የሚያደርግ ነገር በሃሳብህ ፔንት ታደርጋለህ!…” አለቺኝ እንደ ሰዓሊ ሆና ባዶው ሸራ ላይ የሌለ ቡርሽ እያመላለሰች፡፡

ከወዳጄ ጋር ተያየን…

ቀጥለን ደግሞ የዚህን ጉደኛ ስዕል የመሸጫ ዋጋ ከሸራው ግርጌ ዝቅ ብለን አየን…

“30 ሺህ ብር” ይላል፡፡

የባሰ ደነገጥን…

“አልበዛም ዋጋው?…” አልኳት ፈራ ተባ እያልኩ፡፡

ፈገግ አለች…

“ኢት ሲምስ… አርቲስቲካሊ ካላየነው፤ ዋጋው የበዛ ሊመስለን ይችላል!… ፕራይሱ 30 ሺህ የሆነው በምክንያት ነው!… ዋጋው ራሱ አርቲስቲክ ሪፕረዘንቴሽን አለው!… 30,000 ብር ያደረግነው፣ በግራዚያኒ የተጨፈጨፉትን 30,000 ኢትዮጵያውያን ለማስታወስ ነው!… ዩ ጋት ሚ!?…”

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top