Connect with us

ቅዱስ ሲኖዶስ፡ የቀሲስ በላይ መኰንንና ሦስት ግለሰቦችን ሥልጣነ ክህነት ያዘ!

ቅዱስ ሲኖዶስ፡ የቀሲስ በላይ መኰንንና ሦስት ግለሰቦችን ሥልጣነ ክህነት ያዘ!
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

ቅዱስ ሲኖዶስ፡ የቀሲስ በላይ መኰንንና ሦስት ግለሰቦችን ሥልጣነ ክህነት ያዘ!

ቅዱስ ሲኖዶስ፡ የቀሲስ በላይ መኰንንና ሦስት ግለሰቦችን ሥልጣነ ክህነት ያዘ!
~ መንግሥት ለዝቋላ እና ለደብረ ሊባኖስ ገዳማት ጥበቃ እንዲያደርግ ጠየቀ፣

• ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን፣ አባ ገብረ ማርያም ነጋሳ፣ ኀይለ ሚካኤል ታደሰ፣ ቄስ በዳሳ፥ ከነገ የካቲት 11 ቀን ጀምሮ በጥፋታቸው ተጸጽተው ከተግባራቸው በይቅርታ እስኪመለሱ ድረስ ሥልጣነ ክህነታቸው እንዲያዝ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ልዩነት በሌለው ድምፅ ወስኗል፤

• “የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እናዳራጃለን” በማለት በመዋቅር ላይ መዋቅር በመፍጠራቸው እና በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ማኅተም አስቀርፀው በመንቀሳቀሳቸው፣ በአገሪቱ ሕግ ይጠየቃሉ፤

• ያስቀረፁት ማኅተም ገቢ እንዲደረግ፤ የከፈቷቸው ጽሕፈት ቤቶች፥ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም የተከፈቱ እና ሕገ ወጥ በመኾናቸው እንዲዘጉ እንዲደረግ ወስኗል፤

• ኢሬቻንና ዋቄፈናን ከኦርቶዶክስ ክርስትና ጋራ ኾነ ብለው እያመሳሰሉ ለሚያደናግሩ፤ ቤተ ክርስቲያንን ያለስሟ ስም እየሰጡ ለሚተቹ እና በቡድኑ ድጋፍ ለታተሙ መጻሕፍት፥ የሊቃውንት ጉባኤ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በአማርኛ ቋንቋዎች መልስ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶሱ አዟል፡፡

በተያያዘ ዜና፡-

• “በደብረ ዝቋላ የኢሬቻን በዓል እናከብራለን” የሚለው ፖለቲካዊ ቅስቀሳ፥ ሃይማኖትን፣ ታሪክንና የአገርን ሰላም የሚያናጋ በመኾኑ፣ እነኚህ ኀይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፤ ታሪክንና ሰላምን የማስጠበቅ ግዴታ ያለበት መንግሥትም ለገዳሙ ጸጥታዊ ጥበቃ/ከለላ/ እንዲያደርግ ቅዱስ ሲኖዶስ ጠይቋል፣ ጥያቄውም ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እንዲቀርብ ምልአተ ጉባኤው ትእዛዝ ሰጥቷል፤

• ታሪካዊውን የደብረ ሊባኖስ ገዳም፣ የተወሰነ አካል በማድረግ፣ ወገን ሳይለዩ በገዳሙ የሚኖሩ ማኅበረ መነኰሳትን ለማፈናቀል እና ገዳሙን ለመዝረፍ፣ ፍጹም ኢሰብአዊ የኾነ ፖለቲካዊ ማነሣሣት የሚያካሒዱ ኀይሎችን መንግሥት እንዲያስታግሥ እና ለገዳሙም ጸጥታዊ ጥበቃ/ከለላ/ እንዲያደርግ ምልአተ ጉባኤው በጥብቅ ጠይቋል፤

• ቤተ ክርስቲያንን በሐሰተኛ መረጃ እና በጥላቻ ትርክት በማጠልሸት በተጠመዱ የብሮድካስት ብዙኀን መገናኛዎችም ጉዳይ፣ ከብዙኀን መገናኛ ሕግ እና ደንብ አኳያ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ መፈጸም ስላለባቸው ወሳኝ ተግባራት፣ ምልአተ ጉባኤው ዝርዝር መመሪያ መስጠቱ ታውቋል፡፡(ሐራ ተዋህዶ)

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top