Connect with us

ጀዋር መሐመድ ጠ/ሚ ዐብይን ተቸ

ጀዋር መሐመድ ጠ/ሚ ዐብይን ተቸ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ጀዋር መሐመድ ጠ/ሚ ዐብይን ተቸ

~ “እኔን ወደፓርቲ ፖለቲካ የገፉኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው”

ፓለቲከኛው ጀዋር መሐመድ ወደፓርቲ ፓለቲካ የገፉኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የወሰዱት እርምጃ ነው አለ።

ጀዋር ዛሬ ለንባብ ከበቃው አዲስአድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀኝ ዘመም እየሆኑ በሄዱ ቁጥር፣ የሚቃወሟቸውን ማስፈራራት ሲጀምሩ ጠንከር ያለ ተቃዋሚ ያስፈልጋል ወደሚል ገባሁኝ ብሏል።

ጀዋር ጠባቂዎቼ የተነሱትም ቢሾፍቱ ላይ ስለተቃወምኳቸው ነው ማለቱን ጋዜጣው ዘግቧል።

እኔ የኦነግ ልጅ ነኝ፣ ቤተሰቦቼ ኦነጎች ነበሩ ያለው ጀዋር ኢህአዴግን መቀመቅ ከከተቱት ሰዎች አንዱ ነኝ ሲል ለራሱ ምስክርነት ሰጥቷል።

ስለህወሓት በሰጠው አስተያየትም “ከህወሓት ጋር ጠላትም ወዳጅም አይደለንም፤ ህወሓት ተሸንፏል፣ ያሸነፍነውን ድርጅት በወደቀበት መቀጥቀጥ አልፈልግም፣ ከዚያ ባለፈ አጋር ሊሆኑን አይችሉም፣ በአላማም አንድ ልንሆን አንችልም” ብሏል።

በጠ/ሚ እና በህወሓት መካከል ያለው የስልጣን ሽኩቻ ብቻ መሆኑን የገለፀው ጀዋር በአመለካከትና በመርህ ደረጃ ሁለቱ ልዩነት እንደሌላቸው በመጥቀስ ሙስና፣ አፈና አሁንም የቀጠለበትን ሁኔታ በአስረጅነት አንስቷል።

ሽግግሩ በታለመለት መልኩ አልሄደም ሲል የተቸው ጀዋር ብልፅግና ፓርቲ አሀዳዊ መሆኑን፣ ይሄ ደግሞ ለታገለለት የኦሮሞ ሕዝብ አደጋ እንዳለው ተናግሯል።

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top